ዋሺንግተን ዲሲ —
ዋሺንግተንና ቤይጂንግ በአፍሪካ ከፍተኛው የምጣኔ ሃብት ተዋናይ ለመሆን ከባድ ጥረት ይዘዋል።
ቻይና ታዳጊውን የአህጉሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር በያዘችው ጥረት በበርካታ ተቋማት ግንባታ ፕሮጀክቶች እና በውጭ ዕርዳት ላይ በብዙ ቢሊዮኖች የሚገመት ዶላር አፍስሳለች። ዩናይትድ ስቴትስ ግን እነዚህን በመሳሰሉ ጥረቶች ብዙ ርቀት ወደኋላ ናት ሲሉ አንዳንድ ወገኖች ይናገራሉ።
“Plugged in with Greta Van Susteren” በተባለው የቴሌቭዥን ፕሮግራም ላይ በያዝነው ሣምንት የቀረቡት የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ድርጅት ዋና ሥራ አስኪያጅ ማርክ ግሪን ከቻይና ጋር የመጫወቻውን ሜዳ ማስተካከል የሚቻልበትን መንገድ ዘርዝረዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ