በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን የአውሮፕላን አደጋ 20 ሰዎች ሞቱ


በደቡብ ሱዳን ከዩኒቲ ግዛት አየር ማረፊያ ወደ ዋና ከተማ ጁባ ሲያቀና ከተከሰከሰው አውሮፕላን 20 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።
በደቡብ ሱዳን ከዩኒቲ ግዛት አየር ማረፊያ ወደ ዋና ከተማ ጁባ ሲያቀና ከተከሰከሰው አውሮፕላን 20 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።

በደቡብ ሱዳን አንድ አውሮፕላን ተከስክሶ 20 ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ዛሬ ጠዋት አራት ሰዓት ተኩል አካባቢ ‘ዩኒቲ ስቴት’ በተባለው ግዛት ውስጥ በአንድ ነዳጅ ማውጪያ አካባቢ ሲሆን፣ ከአደጋው አንድ ግለሰብ መትረፉም ታውቋል።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው አየር ማረፊያው ሊደርስ 500 ሜትር ያህል ሲቀረው እንደነበርም ተመልክቷል።

የዩክሬኑ የመጓጓዣ አገልግሎት አውሮፕላን በነዳጅ አውጪው ኩባንያ በኪራይ በማገለገል ላይ የነበረ ሲሆን፣ ተሳፋሪዎቹ በሙሉ የኩባንያው ሠራተኞች እንደነበሩም ታውቋል።

አውሮፕላኑ 21 ሰዎችን አሳፍሮ የነበረ ሲሆን፣ አንድ ግለሰብ ግን ሊተርፍ ችሏል።

ከተሳፋሪዎቹ ውስጥ አስራ ስድስት ደቡብ ሱዳናውያን፣ ሁለት ቻይናውያን እና አንድ ህንዳዊ እንደሚገኙበት የኤኤፍፒ ዜና ወኪል ተመልክቼዋለሁ ያለውን የተሳፋሪዎች ዝርዝር ጠቅሷል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG