ዋሺንግተን ዲሲ —
ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ፒትስበርግ በሚገኘው ሲናጎግ ላይ ትኩስ ከፍቶ አሥራ አንድ ሰዎችን በመግደል የተከሰሰው ሰው ዛሬ በዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ቀርቦ ጥፋተኛ አይደለሁም ብሏል። ግድያን፣ የጥላቻ ወንጀልን ያካተቱ 44 የወንጀል ክሶች ቀርበውበታል።
የ46 ዓመት ዕድሜው ሮበርት ባወርስ ፍ/ቤት በቀረበበት ወቅት የቀረቡብትን ክሶች እረዳለሁና ጥፋተኛ አይደለሁም ከማለት በስተቀር ሌላ የተናገረው ነገር እንደሌለ ተዘግቧል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዋና አቃቤ ህግ ጄፍ ሴሽንስ ስለ ክሱ ባስታወቁበት ወቅት ተፈፀሙ የተባሉት ወንጀሎች “የዚህን ሀገር እሴቶችን የማይመጥኑ ከይሲዎችና ዘግናኝ ናቸው” ብለዋል።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ