በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዴንማርክ መርከብ ጊኒ ባህረ ሰላጤ በባህር ላይ ዘራፊዎች ተወረረ


የላይቤሪያ ባንዲራ ያለበት ዘይት ጫኝ መርከብ
የላይቤሪያ ባንዲራ ያለበት ዘይት ጫኝ መርከብ

የዴንማርክ ንብረት የሆነ ነዳጅ ጫኝ መርከብ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ጊኒ ባህረ ሰላጤ ላይ በባህር ላይ ዘራፊዎች መወረሩን የመርከቡ ባለቤት ተናገሩ፡፡ ከዐስራ ስድስቱ የመርከቡ ሠራተኞች ጋራ ግንኙነት የተቋረጠባቸው መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

በላይቤሪያ ባንዲራ የሚጓዘው መርከቡ ከኮንጎ ሪፐብሊክ በስተምዕራብ 260 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ አጣዳፊ አደጋ እንዳጋጠመው የተናገሩት የመርከቡ ባለቤት መርከበኞቹ በደንቡ መሰረት ደህንነታቸው የሚጠበቅበት የመርከቡ ክፍል ውስጥ መደበቃቸውን ገልጸዋል፡፡ የመርከበኞቹን ዜግነት ለመግለጽ አልፈለጉም፡፡

መርከቡ ጥቃት የደረሰበት ዓለም አቀፍ የባህር ክልል ላይ መሆኑ የፖንቴ ኑዋር ወደብ ባለሥልጣን አመልክተዋል፡፡

ከሴኔጋል እስከ አንጎላ የሚዘልቀው እና የ5700 ኪሎ ሜትር ዕርዝማኔ ያለው ዋና የንግድ መርከብ መተላለፊያ መስመር የባህር ዘራፊዎች ጥቃት አደጋ የሚያሰጋበት ሲሆን አብዛኛውን ጥቃት የሚያደርሱት የናይጄሪውያን ወሮበላ ቡድኖች መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG