በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፊሊፒንስ ውስጥ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እየተካሄደ ነው


ምርጫ በፊሊፒንስ
ምርጫ በፊሊፒንስ

በምርጫው ዋናዎቹ ተፎካካሪዎች ከስልጣን የተወገዱት አምባገንን ልጅ እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቿ ናቸው። እአአ በ1986 በህዝባዊ አመጽ ከሥልጣን የተወገዱት የፈርኒናንድ ማርኮስ ልጅ ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር ከምርጫ በፊት በተካሄደ ግምገማ በምራጭ ድጋፍ መርተዋል።

ሆኖም ሌላ ማርኮስ ሥልጣን ላይ ለመውጣት መነሳት የፈጠረውን ድንጋጤ እና ቁጣ ተመርኩዘው ዘመቻ ያካሄዱት ምክትል ፕሬዚዳንቷ ሌኒ ሮብሬዶ በተቀራራቢ ድጋፍ እየተፎካከሩዋቸው ነው። በዛሬው ምርጫ አሸናፊው እአአ ሰኔ 30 ለስድስት ዓመታት ሀገሪቱን የሚመራ ሲሆን ሀገሪቱ ያሉባትን ግዙፍ ችግሮች ይረከባል።

ከችግሮቹ መካከል እጅግ የከበደ ድሕነት እንዲሁም ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ሮድሪጎ ዱቴርቴ ሲያካሂዱት የነበረው እጅግ ጭካኔ የተመላበት ጸረ ሱስ አስያዥ መድሃኒቶች ዘመቻ ይጠቀሳሉ። የፕሬዚዳንቱ ሴት ልጅ ሳራ ዱቴርቴ በምክትል ፕሬዚዳንት ምርጫ ግንባር ቀደም ተፎካካሪ መሆናቸው ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG