በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰው ልጅ አንድ ተጨማሪ እርምጃ በጥልቁ ሰማይ


ፊሌ ተብላ የተሰየመች ንብረትነቷ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ የሆነ መንኩራኩር ሕዋ ውስጥ ከምትገኝ አንዲት ቀደም ብላ ከተላከች የአውሮፓ ኅብረት ማምጠቂያ መደብ ተወንጭፋ በልማድ “ጅራታም ኮከብ” እየተባሉ ከሚጠሩ የተፈጥሮ የሰማይ አካላት ወይም ኮሜቶች በአንዷ ላይ አረፈች፡፡

ፊሌ ተብላ የተሰየመች ንብረትነቷ የአውሮፓ የጠፈር ኤጀንሲ የሆነ መንኩራኩር ሕዋ ውስጥ ከምትገኝ አንዲት ቀደም ብላ ከተላከች የአውሮፓ ኅብረት ማምጠቂያ መደብ ተወንጭፋ በልማድ “ጅራታም ኮከብ” እየተባሉ ከሚጠሩ የተፈጥሮ የሰማይ አካላት ወይም ኮሜቶች በአንዷ ላይ አረፈች፡፡

ተልዕኮው ያለመሣካት ዕድሎች የሰፉበት በብዙ አስጊ ሁኔታዎች እና አደጋዎች ተከብቦ የነበረ ቢሆንም ፊሌ አድራሻዋ ላይ በአዲስ አበባ ጊዜ ከምሽቱ አንድ ሰዓት አካባቢ በድል ስትቀመጥ የሰው ልጅ በዚህ ሁለንተና በሆነው ጠፈር ምርምር ጥረት ውስጥ ታሪክ ሠራ ሲሉ ሳይንቲስቶቹና የአውሮፓ የጠፈር አስተዳደር ባለሥልጣናት በደስታ ፈንድቀዋል፡፡

ሮዜታ የጠፈር መርከብ፤ በሠዓሊ የተሠራ
ሮዜታ የጠፈር መርከብ፤ በሠዓሊ የተሠራ

ሮዜታ ተብላ የምትጠራው የዛሬይቱን አነስተኛ የምርምር መንኩራኩር ተሸክማ ከመሬት የተነሣችው እናት የጠፈር መርከብ ወደ ሰማይ የተለቀቀችው የዛሬ አሥር ዓመት ሲሆን አሁን የምትገኝበትና አነስተኛዪቱን መንኩራኩር ያስወነጨፈችበት ከመሬታችን ስድስት ቢሊዮን ኪሎሜትሮች ርቀት ላይ የደረሰችው ባለፈው ነኀሴ ነበረ፡፡

ሮዜታ የጠፈር መርከብ የምትገኝበት ሥፍራ ከመሬት እስከ ፀሐይ ያለውን ርቀት አርባ ጊዜ ይሆናል፡፡ መሬት ከፀሐይ የምትርቀው ወደ 150 ሚሊዮን ኪሎሜትሮች አካባቢ ነው፡፡

ሮዜታ ላለፉት ሦስት ወራት 67ፒ ቹሪዩመቭ-ጌራሲሜንኮ ተብላ በምትጠራውና (በምኅፃር ኮሜት 67ፒ/ሲ-ጂም ተብላ ትታወቃለች) ሕዋ ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት በምትምዘገዘገው የተፈጥሮ ኮሜት ምኅዋር ውስጥ ገብታ አብራት ስትከንፍና ስትዞራት ቆይታለች፡፡

ከሰባት ሰዓታት ጉዞ በኋላ ኮሜቷ ላይ እንድታርፍ ከእናቲቱ ሮዜታ የጠፈር መርከብ ላይ የተነሣችው ፊሌ መንኩራኩር ዒላማዋ ላይ በሰላም አርፋ ዓለምንና የሳይንሱን ማኅበረሰብ እያስፈነደቀች ነው፡፡

በጠፈር ምርምር ታሪክ ውስጥ የሰው ልጅ በተምዘግዛጊ የሰማይ አካል ላይ የራሱን መሣሪያ ሲያስቀምጥ የዛሬው ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ነው፡፡

ኮሜቷ በጥልቁ ሰማይ ውስጥ የምትከንፈው በሰዓት ከ60 ሺህ ኪሎሜትሮች በላይ በሆነ ፍጥነት ነው፡፡

ኮሜት 67ፒ ቹሪዩመቭ-ጌራሲሜንኮ (ኮሜት 67ፒ/ሲ-ጂ)
ኮሜት 67ፒ ቹሪዩመቭ-ጌራሲሜንኮ (ኮሜት 67ፒ/ሲ-ጂ)

ቅርጿ ወጥ ያልሆነውና ግምድል የአለት ስባሪ የምትመስለው 67ፒ/ሲ-ጂ ትልቀኛው አካሏ ከአንድ ጫፍ ወደ ሌላኛው ያለ የረዥሙ ክፍሏ የአንድ አቅጣጫ ሙሉ ርዝመቷ አራት ኪሎ ሜትር፤ የትንሹ አካሏ 2 ተኩል ኪሎ ሜትር ብቻ ነው፡፡ ጥልቀቷ ከአንድ ጫፍ እስከሌላኛው 3 ኪሎሜትር ነው፡፡

ኮሜት 67ፒ/ሲ-ጂ የገፅታዋ ላይ ሙቀት ከፍተኛው ከዜሮ በታች 43 ዲግሪስ ሴልሽየስ ወይም ከዜሮ በታች 45 ዲግሪስ ፋረንኸይት ሲሆን ዝቅተኛ ሙቀቷ ደግሞ ከዜሮ በታች 68 ዲግሪስ ሴልሽየስ ወይም ከዜሮ በታች 90 ዲግሪስ ፋረንኸይት ነው፡፡

ካዛኽስታን - አልማቲ ላይ በተደረገ ምርምር መስከረም 20/1962 ዓ.ም (በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር) የተገኘችው ኮሜት 67ፒ/ሲ-ጂ የአንድ ዑደት ጊዜዋ በመሬት አቆጣጠር ስድስት ዓመት ተኩል አካባቢ ሲሆን በራሷ እንዝርት ዙሪያ የምታደርገው የሙሉ ዙረት መሾር ደግሞ 12 ሰዓት ተኩል አካባቢ ይፈጃል፡፡

ኮሜት 67ፒ ቹሪዩመቭ-ጌራሲሜንኮ ተብላ የተሰየመችው ባገኟት ሩሲያዊያኑ ወንድና ሴት የጠፈር ተመራማዎች ክሊም ኢቫነቪች ቹርዩመቭ እና ስቬትላና ኢቫኖቫ ጌራሲሜንኮ ስም ነው፡፡

ፊሌ - የጠፈር መሣሪያ፤ በሠዓሊ የተሠራ
ፊሌ - የጠፈር መሣሪያ፤ በሠዓሊ የተሠራ

XS
SM
MD
LG