በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ከፋይዘር ኩባኒያ የኮቪድ መድሃኒት ለመግዛት ሥምምነት ላይ ደረሰች


ፋይዘር ኩባኒያ የሰራው የኮቪድ-19 መድሃኒት
ፋይዘር ኩባኒያ የሰራው የኮቪድ-19 መድሃኒት

ዩናይትድ ስቴትስ ፋይዘር ኩባኒያ ከሰራው አዲሱ የኮቪድ-19 መድሃኒት ለአስር ሚሊዮን ህሙማን የሚበቃ ልትገዛ መስማማቷን ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ።

ሥራ ላይ ለመዋል ፈቃድ እየተጠባበቀ ያለው የፋይዘሩ የኮቪድ መድሃኒት ግዥ በዚሁ የአውሮፓ ዓመተ ምህረት ተጀምሮ በቀጣዩ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

ፕሬዚደንት ባይደን በዋይት ኃውስ ድረ ገጽ ላይ ባወጡት መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ የምግብ እና የመድሃኒት አስተዳደር እና የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ማዕከል ፈቃድ ሲያገኝ በቀላሉ በነጻ መቅረብ እንዲችል አስተዳደራቸው እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።

ፋይዘር ኩባኒያ ባወጣው መግለጫ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ፓክሲሎቪድ የተባለውን መድሃኒት አምስት ነጥብ ሃያ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር ከፍሎ እንደሚገዛ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG