በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጉቴሬሽ በዓለም የፕሬስ ቀን


ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ
ፎቶ ፋይል፦ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ውስጥ ጋዜጠኞች ሥራቸውን በተረጋጋ ሁኔታና ድኅንነታቸው ተጠብቆ እንዲያከናውኑ ለማገዝ መንግሥታት እንዲተጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ጥሪ አስተላለፉ።

“ይህ ወረርሽኝ በዓለሙ ሁሉ ተንሠራፍቶ ባለበት ጊዜ የተሣሣቱ መረጃዎች፣ ጎጂ የጤና ምክሮች፣ እጅግ የተበላሹና አጥፊ ግምታዊ አስተሳሰቦችና መላ ምቶች ሌላ ወረርሽኝ ዓለምን ውጧታል - ያሉት ዋና ፀሐፊ ጉቴሬሽ መገናኛ ብዙኃኑ የተረጋገጡና ሳይንሣዊ መረጃዎችን፣ በማስረጃ የተደገፉ ዜናዎችንና ትንታኔዎችን በማቅረብ እራሱን የቻለ መድኃኒት ይሰጣሉ” ሲሉ አሳስበዋል።

ይሁን እንጂ ወረርሽኙ ከተቀጣጠለ ወዲህ ጋዜጠኞች ለተጠናከሩ ገደቦችና እገዳዎች መጋለጣቸውንና ሥራቸውን ስለሠሩ ብቻ ለበረቱ ቅጣቶችም መዳረጋቸውን ገልፀዋል።

በሃያ ሦስት ሃገሮች ውስጥ ቁጥራቸው ቢያንስ ሃምሣ አምስት የሚደርስ ጋዜጠኞች በኮቪድ-19 ምክንያት መሞታቸውን ጄኔባ የሚገኘው “ፕሬስ ኤምብለም ዘመቻ” አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG