በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በከፍተኛ ደረጃ የጨመረው የናይጄሪያ የነዳጅ ዋጋ


አቡኡጃ፣ ናይጀሪያ
አቡኡጃ፣ ናይጀሪያ

የናይጄሪያ ፕሬዚደንት ቦላ ቲኑቡ የነዳጅ ዋጋ ድጎማውን መሰረዛቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ ትናንት ማክሰኞ ታይቶ በማያውቅ መጠን አሻቅቧል።

ፕሬዚደንቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የነዳጅ ድጎማውን የሰረዙት በሚቆራረጠው የኤሌክትሪክ ኅይል አቅርቦት ምክንያት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የናይጄሪያውያን መኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ድርጅቶች በነዳጅ ላይ በሚተማመኑበት በዚህ ወቅት ነው፡፡

በመንግሥታዊው ብሄራዊ የነዳጅ ልማት ድርጅት (NNPC) ሥር በሚተዳደሩ የነዳጅ ማደያዎች የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ሮይተርስ አገኘሁት ያለውን የውስጥ መረጃ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡

ጭማሪው በናይጄሪያ ገንዘብ፣ በሊትር ከ557 ናይራ ወደ 617 ናይራ ወይም በዩ ኤስ ዶላር ወደ 0.78 ሳንቲም ከፍ ማለቱ ተነግሯል፡፡ባለፈው ዓመት የናይጄሪያን መንግሥት 10 ቢሊዮን ዶላር አስወጥቶታል የተባለው የነዳጅ ድጎማ ከተነሳ ወዲህ ፣ 56 የግል ነዳጅ ተቋማት ከውጭ ነዳጅ የማስመጣት ፈቃድ አግኝተዋል፡፡

ይህም ብሄራዊ የነዳጅ ልማት ድርጅት ገበያውን በብቸኝነት መቆጣጠሩን የሚያስቀር መሆኑ ተገልጿል፡፡ናይጄሪያ ምንም እንኳ ከአፍሪካ ትልቋ የነዳጅ አምራች አገር ብትሆንም፣ በቂ የማጣሪያ አቅም የሌላት እና ያሉትም ተመልካች ያጡ በመሆናቸው፣ ከሞላ ጎደል ጠቅላላውን የተጣራ ነዳጅ የምታስገባው ከውጭ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሮይተርስ የብሔራዊ የነዳጅ ድርጅቱን አስተያየት ለማግኘት እንዳልቻለ አመልክቷል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG