የ3ሺ ሜትር የሴቶች መሰናክል ፍጻሜ ውድድር ዩጋንዳዊቷ ፔሩዝ ቼሜታይ ከዩጋንዳ አሸናፊ ሆናለች። ከርቲኒ ፈሬሪችስ ከዮናይትድ ስቴትስ፣ ሃይቪን ኪያንግ ከኬንያ የብር እና የነሃስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆኑ ኢትዮጵያዊቷ መቅደስ አራተኛ በመውጣት ውድድሯን አጠናቃለች። በአጠቃላይ የሜዳሊያ ብዛት እየመሩ ያሉትን ሀገራት ለመጥቀስ ያህል ዩናይትድ ስቴትስ በ77 ሜዳለዒኣዎች ትመራለች፣ ቻይና እና የሩሲያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ70 እና 53 ሜዳሊያዎች ይከተላሉ።
***
ወደ ሀገሬ ከተመለስኩ ለቅጣት እዳረጋለሁ ያለችው የቤላሩስ አጭር ርቀት ሩጫ ተወዳዳሪ ከጃፓን ወደ ኦስትሪያ መብረሯ ተሰምቷል። ክሪስቲሲና ሲማኖሳካያ ከኦስትሪያ ቬና ሰብዓዊ የይለፍ ወረቀት ወደ ሰጠቻት ፓላንድ በመቀጠል ታቀናለች።
የፖላንድ ጠቅላይ ሞኒስትር ማቲየዝ ሞራዊኪ አትሌቷ በሀገራቸው ካለምንም ክልከላ መኖር እንደምትችል በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል። ሲማኖሳካያ የቤላሩስ ቡድን አባላት ካለ ፍላጎቷ ወደ ሀገሯ ሊመልሷት እየታሩ መሆኑን በመጥቀስ በቶኪዮ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ከለላ እንደጠየቀች ይታወሳል።
ወደ ሀገሯ ብትመለስ በፕሬዚደንት አሌክሳንደር ሉካሺንኮ መንግስት አደጋ ይደርስብኛል ብላ እንደምትሰጋ ከተናገረች በኋላ ሀገራት የድጋፍ እጃቸውን ዘርግተዋል። የቤላሩስን የኦሎምፒክ ኮሚቴ ለ25 ዓመታት የመሩት ፕሬዚደንት ሉካሺንኮ እና ልጃቸው ቪክቶር ነው።