በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፔሩ የቀድሞው መሪ አልቤርቶ ፉጂሞሪ ምሕረት ተሰጣቸው

ፎቶ ፋይል አልቤርቶ ፉጂሞሪ
ፎቶ ፋይል አልቤርቶ ፉጂሞሪ

የፔሩ ፕሬዚደንት ፔድሮ ፓብሎ ኩዢኒስኪ፣ በሰብዓዊ መብት እረገጣና በሙስና ተወንጅለው የ25 ዓመት እስራት ላይ ለሚገኙት ለቀድሞው አምባገነን መሪ አልቤርቶ ፉጂሞሪ፣ ምሕረት መስጠታቸው ተሰማ።

የፔሩ ፕሬዚደንት ፔድሮ ፓብሎ ኩዢኒስኪ፣ በሰብዓዊ መብት እረገጣና በሙስና ተወንጅለው የ25 ዓመት እስራት ላይ ለሚገኙት ለቀድሞው አምባገነን መሪ አልቤርቶ ፉጂሞሪ፣ ምሕረት መስጠታቸው ተሰማ።

ከፕሬዚደንት ኩዢኒስኪ ቢሮ ትናንት ዕሑድ ማምሻው ላይ ይፋ በሆነ መግለጫ መሠረት፣ ምሕረቱ የተሰጠው ከሰብዓዊነት አኳያ ሲሆን፣ መሠረቱም ፉጂሞሪ በማይድን ህመም እንደተያዙ የቀረበው መረጃ መሆኑ ተመልክቷል።

ራሳቸው ፉጂሞሪም፣ ከዓመት በላይ ሆኗቸዋል፣ በጤና መታወክ ምክንያት ምሕረት እንዲደረግላቸው ሲጠይቁ የነበሩት።

ፕሬዚደንት ኩዢኒስኪ ምሕረቱን የሰጡት፣ ከሥልጣን እንዲነሱ ባለፈው ሳምንት የቀረበባቸውን ጥያቄ እንደማይደግፉ ከተቃዋሚ የምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ስምምነት መሆኑን አንዳንድ የፉጆሪ ተችዎች ይናገራሉ።

ፕሬዚደንቱ ከሙስና ጋር በተያያዘ ከሥልጣናቸው እንዲነሱ በርካታ ጥያቄ ቀርቦባቸው እንደበር ተገልጧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG