በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤርትራ በዓለም አንደኛ የፕሬስ ነፃነት ገዳቢ ተባለች


ኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ 15 መካከል ትገኛለች፡፡

የሚድያ ነፃነት ጤናማና ንቁ ኅብረተሰቦች እንዲኖሩ አስፈላጊ ነው ተብሎ ይታመናል፡፡

በዓለም ዙሪያ ገደብ የሌለውን መረጃ ለማግኘት የሰዉ ጥማት እየበረታ በሄደ መጠን አንዳንድ መንግሥታት ያንን ፍሰት ለመገደብ ወይም ለማቆም የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡

ዛሬ ሚያዝያ 25 የዓለም የፕሬስ ነፃነት ወይም ሃሣብን የመግለፅ ነፃነት ቀን ነው፡፡

ከእንግሊዝኛ መጠሪያው ምሕፃር ሲፒጄ እየተባለ የሚታወቀው ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች ደኅንነት ተሟጋች ድርጅት ይህንኑ ዕለት በማስመልከት ይፋ ባደረገው ሪፖርት ሃሣብን የመግለፅ ነፃነትን በብርቱ የሚገድቡ ያላቸውን አሥር ሃገሮች ዝርዝር አውጥቷል፡፡

በዝርዝሩ ላይ በአንደኛ ተራ ቁጥር የሠፈረችው ኤርትራ ስትሆን ተከታዮቿ ሰሜን ኮርያ፣ ሦሪያ፣ ኢራን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ኡዝቤክስታን፣ በርማ፣ ኩባ፣ ቤላሩስና ሣዑዲ አረቢያ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያም ከቻይና፣ ከቱርክሜንስታን፣ ከቪየትናም፣ ከሱዳንና ከአዘርባይጃን ምድብ የምትገኝ ሆና በዝርዝሩ ላይ ከቀዳሚዎቹ አሥራ አምስት መካከል የምትገኝ መሆኑን አንድ የሲፒጄ ሃላፊ ገልጿል፡፡
ዘገባውን ያድምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG