በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ዳግም ስህተት እንዳንሰራ”.. ሥጋት እና ተስፋ በኢትዮጵያ ጉዳይ


አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው
አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው

ሁሉም በየፊናው የሚያምነው ነገር ግን ፈጽሞ የማይገናኝ መንገድ .. “እረ መጨረሻው ምን ይሆን?” .. “ከየትስ ያደርሰን ይሆን?” የሚያስብል ስጋት ማሳደሩ አብዝቶም ማሳሰቡ አይቀር ይሆናል። ይልቁንም በሩቅ ይታዩ የነበሩ ሥጋቶች ደርሰው የየዕለት ክፉ ገጠመኞች መሆን ሲጀምሩ እርግጥም አሳሳቢነቱ ከመቼውም ይብሳል።
“ኑ አሁንም እንሳሳት የሚል ይመስላል የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በኢትዮጵያ ላለው ሁኔታ የሰጠው ምላሽ!” ይላል ስጋትና ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ያዘለው መግለጫ።
እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1991 ዓም ዩናይትድ ስቴትስ የመጀመሪያውን የኢራቅ ጦርነት ለማካሄድ የበቃበችባቸውን ሁኔታዎች መልስ ብሎ የሚመረምር ታሪክ ነው። ከዛሬው የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እና ሥጋቶች ጋር እናዛምደው ዘንድም ይሞግታል። "በጥንቃቄ መፈጸም ያለባቸው" ያላቸውን "ሁነኛ" መንገዶችም ይዘረዝራል።
መጽሄት ለሳምንቱ ወግ መነሻ ባደረገው በዚህ ጽሁፍ ይዘት ዙሪያ ላተኮረው ቃለ ምልልስ እንግዳችን ቶሮንቶ ካናዳ የሚገኘው ለሰብዓዊ መብቶች ከበሬታ የቆመ የትውልደ-ኢትዮጵያውያን ድርጅት ሰብሳቢው አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው ናቸው።

ሙሉ ቃለ ምልልሱን ከዚህ ያዳምጡ።

“ዳግም ስህተት እንዳንሰራ”
please wait

No media source currently available

0:00 0:14:28 0:00

XS
SM
MD
LG