በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ላይ ለመልሶ ጥቅም ያዋለው ፕላስቲክ ከ10 በመቶ እንደሚያንስ ተገለጸ


ፎቶ ፋይል፦ በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ የቶቭላን የቆሻሻ መጣያ ስፍራ እአአ ፌብሩዋሪ 18/2022
ፎቶ ፋይል፦ በእስራኤል በተያዘው ዌስት ባንክ የቶቭላን የቆሻሻ መጣያ ስፍራ እአአ ፌብሩዋሪ 18/2022

በዓለም ላይ ለሥራ ከዋለው የፕላስቲክ መጠን፣ ከ10 በመቶ ያነሰው ብቻ ለመልሶ ጥቅም እንደዋለ የምጣኔ ኃብት ትብብር እና ልማት ተቋም የተሰኘው ድርጅት አዲስ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

“ቅንጅት እና ዓለም አቀፍ መፍትሄ” በተሰኘ ርዕስ ይፋ የተደረገው ሪፖርት ዓለም አቀፍ የፕላስቲክ አጠቃቃም ሥምምነት እንዲኖር ለመጠየቅ በተጠራ ስብሰባ ዋዜማ የወጣ ነው። ሪፖርቱ በ2019 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ብቻ 460 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ፕላስቲክ ለጥቅም ውሏል። ይህ ቁጥር እአአ ከ2000 ወዲህ በእጥፍ መጨመሩን አመላካች ተደርጓል።

የፕላስቲክ ተረፈ ምርት (ግሳንግስ) መጠንም ወደ 353 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በእጥፍ መጨመሩን መቀመጫውን ፓሪስ ላይ ያደረገው ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ 9 በመቶ ብቻ የፕላስቲክ ተረፈ ምርት መልሶ ለሥራ እንደሚውል፣ 19 በመቶው የእሳት እራት እንደሚሆን፣ 50 በመቶው ደግሞ በቀጥታ ወደ ቆሻሻ መጣያ ስፍራዎች እንደሚጋዝ አስረድቷል። ከዚህ በተጨማሪ በ2020 የአውሮፓዊያኑ ዓመት ከቀዳሚው ዓመት ጋር ሲነጻጻር ኮቪድ-19 በመላ ዓለም ሰዎች ፕላስቲክ መጠቀማቸውን በ2.2 በመቶ እንዲቀንሱ እንዳደረጋቸውም ተጠቁሟል።

የዓለም ሙቀት መጠን መጨመር እና የአየር ብክለት ችግሮች በተንሰራፉበት በአሁኑ ሰዓት ሀገራት ለተግዳሮቶች በመቀናጀት እና ዓለም አቀፍ ብልሃቶችን በማግኘት ምላሽ ሊሰጡ እንደሚገባ ተቋሙ አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG