በትግራይ ክልል ራያና አዘቦ ወረዳ ውስጥ ሰባት ሲቪሎች ማንነታቸው ባልታወቀ ታጣቂዎች ትናንት፣ ሰኞ “እንደተገደሉ” የወረዳው አስተዳዳሪ ለቪኦኤ ገለፁ።
አስተዳዳሪው አቶ ተዘራ ጌታሁን መቀሌ ለሚገኘው የቪኦኤ ሪፖርተር ዛሬ፣ ማክሰኞ ማምሻውን በሰጡት ቃል ጥቃቱ የተፈፀመው ድንበር ተሻገረው በገቡ አደጋ ጣዮች መሆኑን ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽንስ ፅህፈት ቤት ዛሬ ማኅበራዊ ገፁ ላይ ባወጣው ፅሁፍ የተገደሉት ሰዎች ከብት ሲጠብቁ የነበሩ መሆናቸውን ጠቁሞ አጥቂዎቹ “ከአፋር ክልል የመጡ ናቸው” ብሏል።
የተገደሉት ሰዎች ማንነትም ሆነ የጥቃቱ ሰበብም አልተገለፀም።
የአፋር ክልላዊ መንግሥትና ፌደራል መንግሥቱ ሁኔታውን እንዲያጣሩና ፍትኅ እንዲስገኙ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጥሪ ማቅረቡን ፅህፈት ቤቱ አመልክቷል።
ቪኦኤ ሁኔታውን በቅርበት ለማጣራት እየሠራ ነው።
በጉዳዩ ላይ ከየትም ሌላ ወገን የተገኘ ተጨማሪ ወይም የተለየ መረጃ የለም።
መድረክ / ፎረም