በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማሊ ሩስያውያን ቅጥር ወታደሮችን እንዳታስገባ ፔንታገን አስጠነቀቀ


A photo published by the Security Service of Ukraine purports to show Wagner Group mercenaries at an unidentified location. (ssu.gov.ua)
A photo published by the Security Service of Ukraine purports to show Wagner Group mercenaries at an unidentified location. (ssu.gov.ua)

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ባለስልጣናት የማሊ የሽግግር መንግሥት በጸጥታ እና በጸረ ሽብርተኛ እንቅስቃሴ ረገድ የሚረዱ ወታደሮችን "ዋግነር ግሩፕ" በሚል ስም ከሚንቀሳቀሰው የሩስያ የግል ወታደራዊ ኩባኒያ ከቀጥራ ከማስገባት እንድትቆጠብ ሲያስጠነቅቁ የከረሙትን ድምጾች ተቀላቅለዋል።

የማሊ መሪዎች ከዋግነር ግሩፕ በየወሩ አስር ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ዶላር በመክፈል የጦር ኃይሉን የሚያሰለጥኑ እና ለከፍተኛ ባለሥልጣናት ጥበቃ የሚሰጡ አንድ ሽህ ወታደሮች ለመቅጠር ስምምነቱን እንዳትፈጽም የዩናይትድ ስቴትስ እና የፈረንሳይ ባለሥልጣናት በይፋ ሲወተውቱ ቆይተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ ማሊ ያን ሥምምነት ብትፈጽም በብዙ መንገድ እንደሚጎዳት አሳስቧል።

የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ሲንዲ ኪንግ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል "የዋግነር ሬኮርድ ሲታይ እነዚህ ሪፖርቶች ዕውነት ከሆኑ ቀድሞውኑም የተዳከመ እና የያልተረጋጋ የሆነውን የማሊን ሁኔታ ማባባሱ አይቀርም" ብለዋል።

ከዚያም በተጨማሪ ማሊ እና ሩስያ ስምምነቱን ካደረጉ የማሊን መንግሥት ለመርዳት ዐለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚሰጠውን ምላሽ ያወሳስበዋል ሲሉም የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚንስቴር ቃል አቀባይዋ አሳስበዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በተለያዩ የሽብርተኛ ቡድኖች የተደቀኑባትን ስጋቶችን መጋፈጥ እንድትችል የሥልጠና እና ሌሎችም ድጋፎች ስታደርግላት ቆይታለች። ሆኖም ዩናይትድ ስቴትስ ያን ድጋፏን በህዝብ የተመረጡትን የሀገሪቱን መሪዎች ከገለበጠው ወታደርዊ መፈንቅለ መንግስት በኋላ አቋርጣዋለች።

ፈረንሳይም ማሊ እና አጎራባቾ ቹዋ ሃገሮች ያሉዋትን ወደ 2000 የሚሆኑ ጸረ ሽብርተኛ ወታደሮች እንደምታስወጣ አስታውቃለች።

የማሊ የሽግግር መንግሥት ከሩስያው ዋግነር ግሩፕ ጋር የጀመርኩት ስምምነት የለም ብሎ አስተባብሉዋል ሆኖም ጠቅላይ ሚንስትሩ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ዩናይትድ ስቴትስ ፈረንሳይ እና ሌሎቹም ሃገሮች ሌላ አማራጭ አልሰጡንም ብለዋል።

XS
SM
MD
LG