በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታጎን ለኢራን ወኪሎች ጠንከር ያለ ምላሽ እንደሚሰጥ ፍንጭ ሰጠ


የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ
የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ

የዩናይትድ ስቴትስ ኃይሎች በመላው መካከለኛው ምስራቅ በኢራን በሚደገፉ ወኪሎች ላይ ከወትሮው ጠንክር ያለ ምት ለመሰንዘር እየተዘጋጁ መሆኑን የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታወቁ፡፡

ጥቃቱ የሚሰነዘረው በዮርዳኖስ በሚገኘው የጦር ሰፈር ላይ በደረሰ የድሮን ጥቃት 3 የአሜሪካ ወታደሮችን ለገደለው እና ከ40 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ለቆሰሉበት ጥቃት ምላሽ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ መግለጫውን የሰጡት እኤአ ጥር 1 በፕሮስቴት ካንሰር ቀዶ ጥገና ምክንያት በተከሰቱ ችግሮች ሳቢያ ሆስፒታል ከገቡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት በሰሜን ምስራቅ ዮርዳኖስ ህንጻ 22 በሚገኘው የመኝታ ክፍሎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት “እጅግ አስከፊ” ብለውታል ። እንደዚያ ያለው ድርጊት የሚታለፍ አይደለም ሲሉም አክለዋል፡፡

ካለፈው የአውሮፓውያን ዓመት ጥቅምት ወር አጋማሽ ጀምሮ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ ከ165 በላይ ጥቃቶች መድረሳቸው ተነግሯል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ እንደ ኋይት ሐውስ እና የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አቻዎቻቸው ሁሉ፣ አሜሪካ በርካታ ዘርፍ ያላቸው ወታደራዊ ርምጃዎችን ሊያካትት በሚችል መልኩ “ባለብዙ ዘርፍ ምላሽ” ለመስጠት እየተንቀሳቀሰች ነው ብለዋል።

ሲቢኤስ የተባለው የአሜሪካ ቴሌቪዥን ትናንት ሐሙስ እንደዘገበው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በኢራቅ እና ሶሪያ ውስጥ "የኢራን ሠራተኞችን እና መገልገያ ተቋማትን" ያካተቱ ዒላማዎች ላይ ለበርካታ ቀናት የሚቆዩ ጥቃቶችን ዕቅድ አጽድቀዋል.

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG