በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታገን ለዩክሬን የሚሰጠው ድጋፍ ተሟጧል


የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን
የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን

የዩናይትድ ስቴትሱ የመከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስቲን ለዩክሬን ድጋፍ የሚሰጠውን ዓለም አቀፍ ቡድን ካቋቋሙበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከሚያዝያ 2022 ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ኪቭ የሩሲያን ወረራ ለመከላከል የሚያስፈልጓትን ሚሳይሎች እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎች አገራቸው መላክ ባልቻለችበት ሁኔታ ውስጥ 50 የሚደርሱትን ሃገራት ወርሃዊ ጉባኤ በማስተናገድ ላይ ነች።

የባይደን አስተዳደር የጠየቀው በጀት እና ለዩክሬን ጦርነት የሚውለውን ተጨማሪ ገንዘብ እንዲያፀድቅ በመጠባበቅ ላይ ባለበት ዩናይትድ ስቴትስ የተፈጠረውን ክፍተት አጋሮቿ እንዲሞሉ ትሻለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ ‘የዛሬው ስብሰባ በረጅም ጊዜ ግቦች ላይ ያተኩራል’ ሲሉ የፔንታጎን ምክትል የፕሬስ ኃላፊ ሳብሪና ሲንግ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። ሲንግ አክለውም፡ "ምንም እንኳን ለደህንነት ጉዳዮች የሚውለውን አስፈላጊ እርዳታ እኛ አሁን መስጠት ባንችልም አጋሮቻችን ግን ያን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል" ብለዋል።

በሌላ ዜና የኔቶ ዋና ፀሃፊ የንስ ስቶልተንበርግ መጠኑ ከ222, 000 በላይ ዙር ለልዩ ልዩ የጦር መሳሪያዎች የሚውሉ ባለ 155 ሚሊ ሜትር ጥይቶች መግዣ የሚውል የ1 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር አዲስ የጋራ ስምምነት መፈራረማቸውን ብራስልስ ላይ አስታውቀዋል።

የተባለው ትጥቅ በሩስያ እና ዩክሬይን ጦርነት በብዛት ጥቅም ላይ ከዋሉት ጥይቶች መካከል ሲሆን፤ የተደረሰውም ስምምነት ኪቭ’ን ለመደገፍ የጦር መሳሪያ ክምችታቸውን ላራቆቱ አጋሮች ክምችታቸውን ለመሙላት የሚውል ነው።

ካለፈው የመስከረም ወር መገባደጂያ አንስቶ በእስራኤል እና በሃማስ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት የመላውን ዓለም ትኩረት ቢሰርቅም፤ ደም አፋሳሹ ሩሲያ በዩክሬን ላይ የከፈተችው ጦርነት ግን አሁንም እንደቀጠለ መሆኑ ይታወቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG