በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታገን አዲሱን ቢ21 ሬይደር ስውር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ይፋ አደረገ


FILE - This undated artist rending provided by the U.S. Air Force shows graphic of the Long Range Strike Bomber, designated the B-21.
FILE - This undated artist rending provided by the U.S. Air Force shows graphic of the Long Range Strike Bomber, designated the B-21.

ዩናይትድ ስቴትስ በሚስጥር የምትገነባው አዲስ ቢ21 ሬይደር (B-21 Raider) ሬይደር የተባለ ስውር የኒውከለር ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ለህዝብ እይታ ይፋ መሆኑ ተነገረ፡፡

አዲሱ ቦምብ ጣይ ከቻይና ጋር ወደፊት ሊኖር ይችላል ለተባለው ግጭት የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን የሚሰጠው ምላሽ አካል መሆኑን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

ቢ21 ሬይደር (ወራሪው ቢ21)የተሰኘውን ስያሜውን ያገኘው እኤአ በ1942 ዱሊትል የተባለው አብራሪ በጃፓን ቶኪዮ ላይ ባደረገው የአየር ወረራ እና ለመጀመሪያ ጊዜ በ30 ዓመታት ውስጥ በሰራው ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ስም መሆኑ ተመልክቷል፡፡

እያንዳንዱ የቢ21 ሬይደር ግንባታ በሚስጥር ተይዞ የቆየ መሆኑም ተነግሯል፡፡ ፔንታገን በፓልምዴል ካሊፎርኒያ ለተጋበዙ ሰዎች ብቻ ዛሬ ዓርብ ቢ21 ሬይደርን ለእይታ የሚያቃምሰ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሬይደርን የሚሰራው መሰረቱን በፎልስ ቸርች ቨርጂኒያ ያደረገው የኖርዝሮፕ ግሩማን ድርጅት ሲሆን የመጀመሪያ በረራውን በሚቀጥለው ዓመት እንደሚያደርግ ተዘግቧል፡፡

ቻይና እአአ በ2035 ወደ 1ሺ500 ዘመናዊ የኒውክለር ጦር መስራያዎች ባለቤት ለመሆን እየተራመደች መሆኑን የጠቀሰው ዘገባ፣ ፔንታገንም ከራዳርና የአየር መቃወሚያ መሳሪያዎች እይታ ውጭ የሆኑ የጦር መሳሪያዎችን በአዳዲስ ቴክኖሎጂ ለማዘመን እየሠራ መሆኑን አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG