በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታገን ለዩክሬን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ

ፋይል - አንድ የዩክሬን ሠራዊት አባል ከኪየቭ፣ ዩክሬን ውጭ በሚገኘው ቦሪስፒል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ የተላከውን እርዳታ የጃቪሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎችን ሲረከብ፤ እኤአ 2/10/2022
ፋይል - አንድ የዩክሬን ሠራዊት አባል ከኪየቭ፣ ዩክሬን ውጭ በሚገኘው ቦሪስፒል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ ከአሜሪካ ወታደራዊ ድጋፍ የተላከውን እርዳታ የጃቪሊን ፀረ-ታንክ ሚሳኤሎችን ሲረከብ፤ እኤአ 2/10/2022

የአሜሪካ መከላከያ መሥሪያ ቤት ፔንታገን ለዩክሬን የተሰጠውን የ 1 ቢሊዮን ዶላር የደህንነት እርዳታ ይፋ አደረገ።

ለጦር መሣሪያና ቁሳቁስ በአንድ ጊዜ ይህን ያህል ድጋፍ ሲሰጥ የሩሲያ ወረራ ከጀመረበት ካለፈው የካቲት ወዲህ ትልቁ መሆኑ ተመልክቷል።

በመከላከያ ሚኒስቴሩ የተገለፀው ይህ እርዳታ ፕሬዚዳንት ባይደን ሥልጣን ከያዙበት ጊዜ አንስቶ ከዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የተሰጠውን ወታደራዊ ደኅንነት ድጋፍ 9.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያደርሰው ተገልጿል።

ሩሲያ “ህገ ወጥ” በተባለ መንገድ ክሬምያን ወደ ራሷ ግዛት ከቀላቀለች አንስቶ ባለፉት ስምንት ዓመታት የተሰጠውን እርዳታ 11.8 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያደርሰው ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG