በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የ1.1 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ ትሰጣለች


"ሂማርስ" የተባለው በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ ተንቀሳቃሽ ሮኬት ተኳሽ፤ በሪጋ ላትቪያ በሚገኘው ስፒልቭ አውሮፕላን ማረፊያ
"ሂማርስ" የተባለው በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ ተንቀሳቃሽ ሮኬት ተኳሽ፤ በሪጋ ላትቪያ በሚገኘው ስፒልቭ አውሮፕላን ማረፊያ

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ለዩክሬን የ1.1 ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ይህም የባይደን አስተዳደር ሥልጣን ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ ለዩክሬን የተሰጠውን አጠቃላይ ወታደራዊ እርዳታ 17 ቢሊዮን ዶላር እንደሚያደርሰው ተመልክቷል፡፡

አዲሱ እርዳታ ዩክሬን በሩሲያ ከተወረረችበት ጊዜ ጀምሮ ግዛቷን ለማስከበር በምታደርገው መከላከል ውጤታማ የሆኑ 18 በምህፃረ ቃል "ሂማርስ" የተባሉትን በከባድ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠሙ ተንቀሳቃሽ ሮኬት ተኳሽ መድፎችንና ጥይቶችን እንደሚጨምር የፔንታንገ ባለሥልጣናት አስረድተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG