በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ እአአ 2019 እሥራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም ታዞራለች

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሜን ኔታንያሁ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሜን ኔታንያሁ

የዩናይትድ ስቴትስ፣ እሥራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን፣ እአአ 2019 መጨረሻ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም እንደምታዞር፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ዛሬ ሰኞ ተናገሩ።

የዩናይትድ ስቴትስ፣ እሥራኤል የሚገኘውን ኤምባሲዋን፣ እአአ 2019 መጨረሻ ላይ ወደ ኢየሩሳሌም እንደምታዞር፣ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ ዛሬ ሰኞ ተናገሩ።

በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ኤምባሲዋን በ2019 መጨረሻ በፊት በማዞር ረገድ ያለውን ዕቅድና ዝግጅት ይጀምራል ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ፣ ፕሬዚደንት ትራምፕ እንደተናገሩት “ኢየሩሳሌም፣ የእሥራኤል ዋና ከተማ ነች፡፡”

ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም ኤምባሲያችንን ከቴልአቪቭ ወደ ኢየራሳሌም የማዘዋወሩን ዝግጅት በቶሎ ያጠናቅቃል ብለዋል ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሬክስ ቲሌርሰን ቀደም ባሉት ቀናት ሲናገሩ፣ ኤምባሲውን የማዞሩ ሥራ ዓመታት ሊወስድ ይችላል ማለታቸው አይዘነጋም።

ኔታንያሁ በበኩላቸው፣ ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ የዩናይትድስ ስቴትስን ኤምባሲ፣ የእሥራኤል ዋና ከተማ ወደሆነችው ኢየሩሳሌም ለማዛወር የወሰዱትን እርምጃ “ታሪካዊ” ብለው ማወደሳቸው አይዘነጋም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG