በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ኮሪያ የክረምት ኦሎምፒክስ የመክፈቻ ሥነ ስርዓት

የደቡብ ኮሪያ የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የአስተናጋጇ የደቡብ ኮሪያ መሪና የሰሜን ኮሪያ መልዕክተኞች
የደቡብ ኮሪያ የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የአስተናጋጇ የደቡብ ኮሪያ መሪና የሰሜን ኮሪያ መልዕክተኞች

ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ዛሬ ዓርብ በተከፈተው የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የአስተናጋጇ የደቡብ ኮሪያ መሪና የሰሜን ኮሪያ መልዕክተኞች አንድ የክብር ትሪቢዩን ተቀመጡ።

ደቡብ ኮሪያ ውስጥ ዛሬ ዓርብ በተከፈተው የክረምት ኦሎምፒክስ ውድድር የመክፈቻ ሥነ ስርዓት ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ የአስተናጋጇ የደቡብ ኮሪያ መሪና የሰሜን ኮሪያ መልዕክተኞች አንድ የክብር ትሪቢዩን ተቀመጡ።

ሆኖም የዩናይትሱ ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ሆን ብለው ከሰሜን ኮሪያው ጋር ከመነጋገር ተቆጥበዋል። ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስና ባለቤታቸው ካረን ባለ ቀይ ሰማያዊና ነጭ ቀለሙን የዩናይትድ ስቴትስ ቲም የክረምት ጃኬት ለብሰው ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዚዳንት ሙን ጄ ኡን ጎን ከጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ ጋር በአንድ መደዳ ተቀምጠዋል ።

የሰሜን ኮሪያ ተወካዮች ኪም ዮንግ ናም እና ኪም ዮ ጆንግ ደግሞ በዚያው ትሪቢዩን ሆኖ ከነሱ ሁለት መደዳ ወደኋላ ባለው ስፍራ ተቀምጠዋል።

ኪም ዮን ጆንግ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ሲሆኑ ዋና አመካሪያቸው ናቸው ። የኮሪያ ጦርነት እአአ 1953 ካበቃ ወዲህ ደቡብ ኮሪያን የጎበኙ የመጀመሪያ የገዢው ቤተሰብ አባል ናቸው።

የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ፔንስ ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ፔንስ እና የፒዮንግንግ ባለሥልጣናት አልተገናኙም አንዳችም ቃል አልተለዋወጡም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG