በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ ለኮቪድ መጋለጣቸው ተሰማ


ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ
ፎቶ ፋይል፦ የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ

የዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፐሎሲ ለኮቪድ-19 መጋለጣቸውን ዛሬ ተገለጠ።

የሰማንያ ሁለት ዓመቷ አፈ ጉባዔ ትናንት ረቡዕ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በነበሩበት አንድ ዝግጅት ላይ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ ሳያደርጉ ተገኝተው እንደነበር ተዘግቧል።

ምንም የህመም ስሜት እንደሌላቸው እና ራሳቸውን ለይተው እንደሚቆዩ ነው የተገለጸው።

ቃል አቀባያቸው ድሩው ሃምል ዛሬ በሰጡት ቃል "አፈ ጉባዔ ፐሎሲ የኮሮናቫይረስ መከላከያ ሙሉ ክትባታቸውን ወስደዋል። ማጠናከሪያውንም መከተባቸውን እና በክትባቱ ከህመም ስለጠበቃቸው ከህመም ደስተኛ ናቸው" ብለዋል።

ወደእስያ ሊደረግ ታቅዶ የነበረ የምክር ቤት አባላት ጉብኝት ወደሌላ ግዜ እንደሚተላለፍ ቃል አቀባያቸው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG