በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግሥት መ/ቤቶች ካልተከፈቱ የትራምፕ ዓመታዊ ንግግር ይዘግይ ተባለ

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ
የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በከፊል የተዘጉት የመንግሥት መ/ቤቶች በያዝነው ሳምንት ካልተከፈቱ በስተቀር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስለሀገሪቱ ሁኔታ የሚያደርጉት ዓመታዊ ንግግር መዘግየት አለበት ወይም ደግሞ በፁሑፍ ያሰሙት የሚል ሃስብ አቅርበውል።

የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በከፊል የተዘጉት የመንግሥት መ/ቤቶች በያዝነው ሳምንት ካልተከፈቱ በስተቀር ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ስለሀገሪቱ ሁኔታ የሚያደርጉት ዓመታዊ ንግግር መዘግየት አለበት ወይም ደግሞ በፁሑፍ ያሰሙት የሚል ሃስብ አቅርበውል።

ፔሎሲ ይህን ሃሳብ ያቀርቡት እአአ ጥር 29 እንዲደረግ የታቀደው ፕሬዚዳን ትረምፕ በሀገሪቱ ምክር ቤት ቀርበው የሚያደርጉት ዓመታዊ ንግግር የፀጥታ ጥበቃ ዝግጅት ስለሚያስፈልገው እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ፔሎሲ ለትረምፕ በላኩት ደብዳቤ “ፕሬዚዳንቱንና ቤተሰቦቻቸውን የሚጠብቁት የሀገሪቱ ሚስጢራዊ አገልግሎት ሰራተኞች እንዲሁም የአገር ውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር ከፊል የመንግሥት መ/ቤቶች ከተዘጉበት ጊዜ አንስቶ ክፍያ አላገኙም” ሲሉ አሳስበዋል።

ፕሬዚዳንቱን የሚጠብቁት የፀጥታ ሰራተኞች እአአ ከታህሳስ 22 ቀን አንስቶ ካለክፍያ ነው የሚሰሩት።

የአገር ውስጥ ደኅንነት ጥበቅ ሚኒስትር ክረስቲጄን ኔልሰን ግን “አገልግሎቶቹ የዓመታዊ ንግግሩን ሂደት ለመጠበቅና ለመደገፍ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ናቸው” ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG