የሽሪ ላንካ’ው ፕሬዝዳንት አኑራ ኩማራ ዲሳናያኬ አዲሱ የማርክሳዊ ርዕዮት ዘመም ፓርቲ በብሄራዊው ሸንጎ ምርጫ አብላጫ ድምጽ ማግኘቱን ዛሬ አርብ ይፋ የተደረገው የምርጫ ውጤት አረጋገጧል። ፕሬዝዳንቱ የምጣኔ ሃብት ተሃድሶ ለማድረግ ለወጠኑት መርሃ ግብራቸው ብርቱ ድጋፍን መስጠቱ ተመልክቷል።
የሃገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ባደረገው በዚህ ከፊል የምርጫ ውጤት መሠረት የዲሳናያኬ ‘ብሔራዊ የሕዝቦች ኃይል’ ፓርቲ ከፓርላማው 225 መቀመጫዎች 123ቱን ሲያሸንፍ፤ ሳጂት ፕሪሜዳሳ የሚመሩት ተቃዋሚው የተባበሩት ሕዝቦች ኃይል ፓርቲ በበኩሉ 31 መቀመጫዎች አሸንፏል።
ዲሳናያኬ ሽሪላንካውያን ከእንግሊዝ ቅኝ አገዛዝ ነጻ ከወጣችበት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር 1948 አንስቶ ደሴቲቱን አገር ያስተዳደሩትን፣ የተለመደ የፖለቲካ አሰራር የሚከተሉ ፓርቲዎች ትቶ በከፍተኛ ድጋፍ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሆነው ባለፈው መስከረም ወር አጋማሽ መመረጣቸው ይታወሳል።
መድረክ / ፎረም