ዳሸን ቢራ፣ ቫሳሪ ግሎባልና ዱዌት ግሩፕ ከተባሉት የብሪታንያ ኩባንያዎችና ጥረት ግሩፕ ከተባለው የኢትዮጲያ ኩባንያ ጋር በመተባበር የቢራ ፋብሪካውን የከፈተው ደብረ ብርሀን ከተማ ላይ ነው። ዳሸን ኢትዮጵያ ውስጥ ግዙፍ ከሚባሉት የቢራ ፋብሪካዎች አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ የመክፈቻውን ስነ ስርአት መርተው ባደረጉት ንግግር የአዲሱ የቢራ ፋብሪካ መከፈት ሀገሪቱ አለም አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት የማዳበር ብቃት እንዳላት ያመለክታል ብለዋል።
ዱዌት፣ ቫሳሪና ጥረት የተባሉት የብሪታንያና የኢትዮጵያ ኩባንያዎች ለጋራ ብልጽግና አብረው ሊሰሩ እንደሚችሉ አሳይተዋል። እንዲህ አይነቱ መልካም ተግባር ሊገፋበት ይገባል።የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ
የቢራ ኩባንያው መከፈት በኢትዮጵያ የሚታየውን የቢራ ተፈላጊነት በሀገሪቱ የመካከለኛው መድብ መበራከትንና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ጤናማ ይዘትን ያመላክታል ሲሉ የኩባንያው አጋር ባለቤቶች አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ የመጠጥ ዘርፏን ለአለም አቀፍ መዋዕለ-ነዋይ ፍሰት የከፈተች ቢሆንም ቴልኮምን የመሳሰሉት ኢንዱስትሪዎች በመንግስት እጅ መሆናቸው ቀጥሏል። ባንኮችና በቀጥታ
ለሸማች የሚያቀርቡ ቢዝነሶች ደግሞ ለውጭ ተቀላጆች አይፈቀዱም። ዘገባውን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።
በተጨማሪም ከዚህ በታች ያለውን ቪድዮ ይመልከቱ።