በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በከፊል ከተዘጋ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል


የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በከፊል ከተዘጋ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ቢይዝም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በዴሞክራቲክ እንደራሴዎች መካከል መግባባት ላይ ስለመደረሱ የታየ ፍንጭ የለም።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት በከፊል ከተዘጋ ዛሬ ስድስተኛ ቀኑን ቢይዝም በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕና በዴሞክራቲክ እንደራሴዎች መካከል መግባባት ላይ ስለመደረሱ የታየ ፍንጭ የለም።

ፕሬዚዳንቱ በሜክሲኮና በዩናይትድ ስቴትስ ወሰን ላይ የግንብ አጥር ለማቆም የጠየቁትን የአምስት ቢሊዮን ዶላር ወጭ ያካተተ የመንግሥታቸውን በጀት ዴሞክራቶቹ በመቃወማቸው በገቡበት መፋጠጥ ነው መንግሥቱ ሥራዎቹን በከፊል ለማቆም የተገደደው።

የአጥሩን ሃሣብ የተቃወሙት የዴሞክራቶቹ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት ፍላጎት “ለወሰን ደኅንነት ማስጠበቂያ የተለያዩ ክንዋኔዎች መዋል አለበት” ያሉት የ1.3 ቢሊዮን ዶላር ወጭ ለፕሬዚዳቱ እንዲለቀቅላቸው ነው።

ሚስተር ትረምፕ ዛሬ ባወጡት የትዊተር መልዕክት “በደቡብ ድንበራችን ላይ የወሰን ደኅንነትና አጥር በብርቱ እንደሚያስፈልገን ዴሞክራቶቹ በስተመጨረሻ እንዲገነዘቡ ንገሩልኝ” ብለዋል።

በዝጉ ጊዜ አብዛኞቹ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ እንደይከፈላቸው የተደረጉትም “በዴሞክራቶቹ ምክንያት ነው” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ የአፅንዖት ቃል አስፍረዋል።

መንግሥቱ ዝግ ሆኖ እስከመቼ እንደሚቆይ ትናንት የተጠየቁት ትረምፕ “የፈጀውን ያህል ጊዜ፤ አጥር ይኖረናል፤ ደኅንነት ይኖረናል” ሲሉ መልሰዋል ለጋዜጠኞች።

ከአምስት ቢሊዮን ዶላሩ ጥያቄያቸው አፈግፍገው ለወሰን ደኅንነት ቀነስ ያለ ቁጥር ይቀበሉ እንደሆነ ቢጠየቁም በዚያ ላይ ሃሣባቸውን መግለፅ አልፈለጉም።

ፕሬዚዳንቱ “ሃገሪቱን ወደ ቀውስ እየዘፈቋት ነው” ሲሉ ዴሞክራቶቹ ይከስሳሉ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG