በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ም/ቤት አባላት አዲስ ባጀት ውይይት


ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥትና የምክር ቤት አባላት በአዲሱ ባጀት ላይ ካልተስማሙ ከመጪው አርብ እኩለ ሌሊት አንስቶ አንድ አራተኛው የመንግሥት ሥራ ሊዘጋ ይችላል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የዋይት ኃውስ ቤተ መንግሥትና የምክር ቤት አባላት በአዲሱ በጀት ላይ ካልተስማሙ ከመጪው አርብ እኩለ ሌሊት አንስቶ አንድ አራተኛው የመንግሥት ሥራ ሊዘጋ ይችላል።

በጀቱ ፕሬዚዳንት ትረምፕ የጠየቁትን ከሜክሲኮ ጋር በሚዋስነው ድንብር ግምብ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ገንዘብ ያካትታል ወይም አያካትም ማለት ነው። ፕሬዚዳንቱ ግንብ እንዲሰራ የሚፈልጉት ህገወጥ ፍልሰተኞችን ለመከላከል ነው።

ሶስት አራተኛው የመንግሥት ሥራን እስከ መጪው መስከረም ወር የሚያንቀሳቅሰው በጀት ጸድቋል። ገና ያልፀደቀው የመጪው ዓመት የአገር ውስጥ ደኅንነት ጥበቃ ሚኒስቴር በጀትንና ለግንቡ የሚሆን ገንዘብን ያካትታል።

ፕሬዚዳንት ትረምፕ እንዲገነባ ለሚፈልጉት $5 ቢልዮን ዶላር ለሚፈጀው ግንብ የጠየቁት መያዣ ገብዘብ $5 ቢልዮን ዶላር ሲሆን ዲሞክራቶችና አንዳንድ ሪፖብሊካውያን አጥብቀው ይቃወሙታል። ዲሞክራቶች በበኩላቸው የድንበር ፀጥታን ለማጠናከር የ $1.6 ቢልዮን ዶላር ባጀት ለመመደብ ሃሳብ አቅርበዋ።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG