በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓርላማው የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትንና የምክትላቸውን ሹመት አጸደቀ


ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ
ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ

የቀድሞውን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ያለመከሠሥ መብት አነሣ

የኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝን የከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት፤ ወ/ሮ ዘሃራ ዑመርን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ሾሟል።

ወ/ሮ ሌሊሲ ደሳለኝ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩ ሲኾን፣ ወ/ሮ ዘሃራ ዑመር ደግሞ፣ በሶማሌ ክልል በተለያዩ ደረጃዎች፣ በዳኝነት እና በሌሎችም ሕግ ነክ አገልግሎቶች ያገለገሉ ናቸው፡፡

ወ/ሮ ዘሃራ ዑመር
ወ/ሮ ዘሃራ ዑመር

በሌላ በኩል ምክር ቤቱ፣ የቀድሞ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የነበሩትን የተወካዮች ምክር ቤት አባል፣ ዶር. ጫላ ዋታ ያለመከሠሥ መብት አንሥቷል፡፡

ያለመከሠሥ መብታቸው የተነሣው ዶር. ጫላ፣ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በነበሩበት ወቅት፣ ፈጽመዋቸዋል በተባሉ የተለያዩ የሙስና ተግባራት፣ በመንግሥት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል፤ በሚል፣ የፍትሕ ሚኒስቴር ያቀረበውን ጥያቄ ተከትሎ እንደኾነ ማብራሪያ ተሰጥቶበታል።

ዶር. ጫላ ዋታ፣ ያለመከሠሥ መብታቸው በእንደራሴዎች ምክር ቤቱ መነሣቱን ተከትሎ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG