በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቤልዥግ ፖሊሶች ባካሄዱት አሰሳ የፓሪስ ተጠርጣሪ አሻራ ማግኘታቸውን አስታወቁ


በአንድ የብራስልስ አፓርትመንት ውስጥ ባካሄዱት አሰሳ፣ እአአ ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ተጠርጣሪ ነው ያሉትን ሰው አሻራ ማግኘታቸውን ዛሬ ዐርብ አስታወቁ።

የቤልዥግ ፖሊሶች፣ በአንድ የብራስልስ አፓርትመንት ውስጥ ባካሄዱት አሰሳ፣ እአአ 2015 ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ለደረሰው ጥቃት ተጠርጣሪ ነው ያሉትን ሰው አሻራ ማግኘታቸውን ዛሬ ዐርብ አደረጉ።

የቤንዢግ ፌዴራላዊ መንግሥት ዐቃቤ ህግ ቢሮ እንዳስታወቀው፣ መርማሪዎች ሳላሕ አብደሰላም (Salah Abdeslam) የተባለውን ተጠርጣሪ አሻራና፤ ምናልባትም ፈንጂዎችን ለመያዝ የሚያገለግሉ ሊሆኑ ይችላሉ ያሏቸውን ሦስት የእጅ ሥራ የሆኑ ቀበቶዎችን አግኝተዋል። በዚሁ መኖሪያ ህንፃ ውስጥ መርማሪዎቹ የፈንጂ ምልክቶችንም እንዳገኙ ተናግረዋል።

ሳላሕ አብደሰላም (Salah Abdeslam)
ሳላሕ አብደሰላም (Salah Abdeslam)

ተጠርጣሪው አብደሰላም (Abdeselam) ወደተጠቀሰው አፓርትሜንት መቼ እንደገባ ግልጽ አለመሆኑን ያመለከተው የዐቃቤ ህጉ ቃል-አቀባይ፣ ባለሥልጣናቱት ደግሞ አሁን የተገኘውን ውጤት ይፋ ለማድረግ ስለምን አንድ ወር ሙሉ እንደቆዩ አላብራራም።

እአአ 2015 ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ጥቃት የተከሰተባቸው ቦታዎች
እአአ 2015 ባለፈው ኅዳር 13 ቀን ፓሪስ ውስጥ ጥቃት የተከሰተባቸው ቦታዎች

XS
SM
MD
LG