በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓሪስ ጥቃት ያደረሰውን ግለሰብ ምክንያት የሚያብራራ ቪዲዮ ይፋ ተደረገ


ፓሪስ ውስጥ በሚገኘው አይፍል ታወር አካባቢ ወታደሮች አካባቢው በመጠበቅ ላይ እአአ ኅዳር 3/2023
ፓሪስ ውስጥ በሚገኘው አይፍል ታወር አካባቢ ወታደሮች አካባቢው በመጠበቅ ላይ እአአ ኅዳር 3/2023

ፓሪስ ውስጥ በሚገኘው አይፍል ታወር አካባቢ አንድ ቱሪስት በስለት ወግቶ የገደለው ግለሰብ በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ ባሰራጨው የቪዲዮ ምስል ለእስላማዊ መንግስት ቡድን ያለውን ታማኝነት መግለፁን፣ የፈረንሳይ ፀረ-ሽብር አቃብያነ ህግ እሁድ እለት አስታወቀ።

ባለስልጣናት እስላማዊ አክራሪ መሆኑ እና በቅርብ ጊዜ በፈረንሳይ የደረሱ ጥቃቶችን ከፈፀሙ አካላት ጋር በማህበራዊ ሚዲያ ግንኙነት እንደነበረው ያስታወቁት ግለሰብ የአይምሮ ጤና እክል እንደነበረበት እና ጥብቅ የስነ-ልቦና ክትትል ይደረግለት እንደነበር ከፍተኛ አቃቤ ህግ ዣን ፍራንስዋስ ሪካርድ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የግለሰቡም እናት ጥቅምት ወር ላይ የልጇ ነገር እንዳሳሰባት አሳውቃ የነበር ቢሆንም፣ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል በቂ ማስረጃ እንዳልነበርም አክለው ገልፀዋል።

ቅዳሜ መገባደጃ ላይ በቢላዋ ጥቃቱን ማድረሱ የተገለፀው አርማንድ ራጃፑር-ሚያንዶአብ፣ እ.አ.አ በ1997 ከኢራናዊ ወላጆቹ ፈረንሳይ ውስጥ የተወለደ ሲሆን የጀርመን ዜግነት ያለው የ23 አመት ወጣት ቱሪስት ወግቶ ሲገድል ሌሎች አራት ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል። አንድ የታክሲ ነጂ ጣልቃ ከገባ በኃላም፣ "አላሁ አክበር" ሲል በመጮህ ለመሰወር ሲሞክር በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።

ራጃፑት-ሚያንዶአብ ጥቅምት ላይ፣ ቀደም ሲል ትዊተር ተብሎ ይጠራ በነበረው ኤክስ ማህበራዊ ድህረ ገፅ ላይ በከፍተው ገፁ ስለሐማስ፣ ጋዛ እና ፍልስጤም በብዛት ይፅፍ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ በዚሁ ገፅ ላይ በአረብኛ ባስልተላለፈው የቪዲዮ ምስል እራሱን አፍጋኒስታን ውስጥ እንደሚገኝ የእስላማዊ መንግስት ተዋጊ አድርጎ ማቅረቡ ተመልክቷል። ለእስላማዊ መንግስት ታማኝነቱን በመግለፅም በአፍሪካ፣ በኢራቅ፣ ሶሪያ፣ የመን እና ፓኪስታን ለሚገኙ ጂሃዲስቶችም ድጋፉን ገልጿል።

ከጥቃቱ ጋር በተያያዘ ራጃፑት-ሚያንዶአብን ጨምሮ፣ በጥቃት አድራሹ ዙሪያ የሚገኙ ሶስት ሰዎች እሁድ እለት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አቃቤ ህጉ አስታውቀዋል።

እሁድ እለት ከተካሄደ የደህንነት ስብሰባ በኃላ መግለጫ የሰጡት የፈረንሳይ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጀራልድ ዳርመኒን በሰጡት መግለጫ፣ የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባቸው እና አክራሪ ናቸው ተብለው ለሚታመኡ ሰዎች ባለስልጣናት "አስገዳጅ የአይምሮ ጤና ህክምና መጠየቅ መቻል አለባቸው" ብለዋል።

ፈረንሳይ "የረጅም ጊዜ አክራሪ እስላማዊ ስጋት ውስጥ ትቆያለች" ሲሉም "በጣም ጠንካራ የቅጣት ምላሽ" እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG