በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታጣቂዎች በዳርፉር ያደረሱት ጥቃት 'የዘር ማጥፋት' ሊባል ይችላል - ሂዩማን ራይትስ ወች


ፎቶ ፋይል፦ ግጭቱ በቀጠለበት የምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ በሆነችው በኤል ጄኔና ገበያ ውስጥ ሰዎች ይንቀሳቀሳሉ እአአ ሚያዝያ 29 2023፣
ፎቶ ፋይል፦ ግጭቱ በቀጠለበት የምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ በሆነችው በኤል ጄኔና ገበያ ውስጥ ሰዎች ይንቀሳቀሳሉ እአአ ሚያዝያ 29 2023፣

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በዋናነት አረብ ሚሊሺያ የሆኑ አጋሮቹ፣ ምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል-ጄኔና ውስጥ የሚገኙ የማሳሊት ተወላጆችን እና ሌሎች አረብ ያልሆኑ ማህበረሰቦችን ዒላማ በማድረግ ለተፈጸመው የዘር ማጽዳት ዘመቻ ተጠያቂ መሆናቸውን ዓለም አቀፉ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድን ሂዩማን ራይትስ ወች አስታወቀ።

የሰብዓዊ መብት ተቋሙ "ማሳሊቶች ወደ ቤት አይመለሱም፡ በምዕራብ ዳርፉር ኤል-ጄኔና ውስጥ የተፈጸሙ የዘር ማጽዳት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች" በሚል ርዕስ ሐሙስ እለት ይፋ ባደረገው 186 ገፅ ያለው ሪፖርት፣ "በማሳሊት እና ሌሎች አርብ ባልሆኑ ህዝቦች ላይ የዘር ማፅዳት ዘመቻ" መፈፀሙን አመልክቷል።

ማሳሊቶች ወደ ቤት አይመለሱም፡ በምዕራብ ዳርፉር ኤል-ጄኔና ውስጥ የተፈጸሙ የዘር ማጽዳት እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች"

የፈጥኖ ደራሹ ኃይሎች እ.አ.አ ከሚያዚያ 2023 ጀምሮ ከአገሪቱ ጦር ኃይሎች ጋር በሚያደርጉት ጦርነት፣ ከሌሎች አጋር አረብ ሚሊሺያዎች ጋር በመሆን የዘር ማጽዳት፣ በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን እና የጦር ወንጀሎችን ፈፅመዋል የሚል ክስ ይቀርብባቸዋል። ጦርነቱ ኤል-ጄኔና ውስጥ የተገደሉትን 15 ሺህ ሰዎች ጨምሮ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

ሂዩማን ራይትስ ወች በሪፖርቱ እ.አ.አ በሚያዚያ እና በሰኔ 2023 ዓ.ም ለሰባት ሳምንታት የተካሄዱ የጥቃት ዘመቻዎችን እና የስቃይ ተግባራትን በዝርዝር ያቀረበ ሲሆን፣ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ፈጥኖ ድራሹ ታጣቂ ኃይል እና አጋሮቹ "የማሳሊት ነዋሪዎችን በመግደል እና በማሳደድ ስልታዊ ዘመቻ አካሂደዋል" ሲል በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎች ግድያ ተጠያቂ መሆናቸውን ገልጿል።

ጥቃቱ የጅምላ ማሰቃየትን፣ አስገድዶ መድፈርን እና ዘረፋ የመሳሰሉ አሰቃቂ ድርጊቶችን እንደሚያካትት የጠቀሰው ሪፖርት፣ በሰኔ አጋማሽ ላይ ተባብሶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በቀናት ውስጥ መገደላቸውን አመልክቷል። ጥቃቱ እንደገና በህዳር ወርም ማገርሸቱንም ጠቅሷል።

የአካባቢው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጠበቃዎች በጥቃቱ ዶክተሮችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቶችን፣ የአካባቢ መሪዎችን እና የመንግስት ባለስልጣናትን ጨምሮ "ታዋቂ የማሳሊት ማህበረሰብ አባላት" ዒላማ መደረጋቸውን አመልክተዋል።

ሂዩማን ራይትስ ወች አክሎ አጥቂዎቹ በተለይ የተፈናቀሉ ማሳሊቶች በሚገኙባቸው አካባቢዎች "ወሳኝ የሲቪል መሠረተ ልማቶችን ሆን ብለው ማውደማቸውን" ገልጿል። የሳተላይት ምስሎች፣ ከሰኔ ወር ጀምሮ በዋናነት ማሳሊቶች በሚኖሩባቸው የኤል-ጄኔና አካባቢዎች "የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደቤታቸው እንዳይመለሱ መኖሪያ መንደራቸው ሆን ተብሎ በቡልዶዘር መመንጠሩን" እንደሚያሳዩ ሪፖርቱ አመልክቷል።

ግድያዎቹ፣ "ፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና አጋሮቻቸው ቢያንስ በምዕራብ ዳርፉር የሚገኘውን የማሳሊት ማህበረሰብ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የማጥፋት ዓላማ እንዳላቸው ያሳያል" ያለው የሂዩማን ራይትስ ወች ሪፖርት ይህም የዘር ማጥፋት መፈጸሙን ወይም እየተፈጸመ መሆኑን የሚያመለክት ነው ብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG