በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የነገይቱ ኢትዮጵያ የዛሬ መንገዶች


መስፍን ነጋሽ፣ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ፣ ሄኖክ የማነ
መስፍን ነጋሽ፣ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ፣ ሄኖክ የማነ

“ዶ/ር አብይ ‘እንዲህ ማድረግ አለበት፣ እንዲህ ማድረግ አለበት’ የሚለውን ሳይ፤ የችግሩን መጠን የተረዳን አይመስለኝም።” ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ። “.. የተወሰኑ በዝርዝር ሊነግረን የማችልም የማይገቡም ነገሮች መኖራቸውን እረዳለሁ። .. ወደ ፊት መሄድ አለብን እያልን ነው። ነገር ግን ወደ ፊት መሄዳችንን በምንድን ነው የምንረዳው?” መስፍን ነጋሽ። “ኢሐዴግ እንደ ፓርቲ ሁለት ዛፍ ላይ ለመውጣት የተገደደ ይመስለኛል።” ሄኖክ የማነ።

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይዞታና ቀጣይ አቅጣጫ፣ ወግ ያለው ፍተሻ” … የውይይቱ ትኩረት ነው። ሰሞንኛውን አበይት የፖለቲካ ጉዳዮች ምንነትና አንድምታ በመዳሰስ የሚንደረደረው ውይይት፣ የነገዪቱን ኢትዮጵያ መዳረሻ መሠረቶች እና ከዚያ የሚያደርሱ ጎዳናዎች ጠበቅ አድርጎ ይመረምራል። በሂደቱ የሚታዩትን ፈተናዎችም ይቃኛል።

ተወያዮች፡- በዚህ በዩናይትድ ስቴትስ የኦሃዮ ክፍለ ግዛት የሚገኘው የዴይተን ዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና መምህሩ ፕሮፌሰር መሳይ ከበደ፤ ከስቶክሆልም ስዊድን የዋዜማ ራዲዮው መስፍን ነጋሽ እና እንዲሁም በስቴት ኦፍ ኒው ዮርክ ዩኒቨርሲቲ የድሕረ ምረቃ ፕሮግራም የፍልስፍና ትምሕርት በመከታተል ላይ የሚገኘው ሄኖክ የማነ ናቸው። የውይይቱን ተከታታይ ክፍሎች ከዚህ ያድምጡ።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

please wait

No media source currently available

0:00 0:25:38 0:00
የነገይቱ ኢትዮጵያ የዛሬ መንገዶች - ሁለተኛውን ክፍል ከዚህ ያድምጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:51 0:00
የነገይቱ ኢትዮጵያ የዛሬ መንገዶች - የውይይቱን የመጨረሻ ክፍል ከዚህ ያድምጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:53 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG