በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓንዶራ ሰነዶችና ዓለም አቀፉ ሙስና


የፓንዶራ ሰነዶችና ዓለም አቀፉ ሙስና
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:29 0:00

የፓንዶራ ሰነዶችና ዓለም አቀፉ ሙስና

የዓለም መሪዎች፣ የፖለቲካ ሰዎች እና ታዋቂ የፖፕ ሙዚቃ አቀንቃኞች፣ ማንነታቸው ባልታወቁ ድርጅቶች ስምና መረቦች አማካይነት፣ ትላልቅ ሀብቶቻቸውን እያሸሹ ከሚደብቁ፣ በሺዎች ከሚቆጠሩ ሰዎች መካከል መሆናቸው ተጋልጧል፡፡

ሾልኮ የወጣውን ድርጊት ያጋለጠው ፣ ፓንዶራ ፔፐር የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ 12 ሚሊዮን ፋይሎችን ፣ ከበርካታ የህግ ተቋማት አሰባስቧል፡፡

ይህ “ከባህር ማዶ ባለው ምስጢራዊው የፋይንስ ዓለም ላይ ብርሃንን የፈነጠቀ ነው፡፡” ተብሏል፡፡

አስደንጋጭ ከሆኑት የፓንዶራ ፔፐር ድብቅ የሀብት ክምችት ዝርዝር ውስጥ፣ የአዘርባጃኑ ፕሬዚዳንት ኤሃም አሊቭ እና ቤተሰቦቻቸው አንዱ ነው፡፡

ሾልኮ የወጣው ሰነድ እንደሚያሳየው፣ የአሊቭ ቤተሰብና ተባባሪዎቻቸው ባላፉት 15 ዓመታት ፣ እንግሊዝ ውስጥ በንግድ ያንቀሳቀሱት ሀብት፣ ከ544 ሚሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡

ርቸል ዴቪስ ተካ፣ ዓለም አቀፉ የግልጽነትና ጸረ ሙስና ዘመቻ፣ የእንግሊዙ ተሟጋች ቡድን ኃላፊ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ይህ ቤተሰብ ሥልጣን ከተረከበበት እኤአ 1993 አንስቶ የአገሪቱ ዋነኛ የእንደስትሪና ተፈጥሯዊ ሀብቶች በመቆጣጠር በርካታ ሀብት አከማችተዋል፡፡ ይህ የሆነው በአገሪቱ በህዝብ ጫንቃ ላይ ነው፡፡ እነዚህ የአገሪቱን ህዝብ ሳይበድሉ የተፈጸሙ አይደሉም፡፡ ለአገሪቱ ዜጎች መከፋፈል የነበረባቸው እነዚህ ሀብቶች በመሪዎቻቸው በመነጠቃቸው ሳቢያው የሚሰቃዩ በርካታ ሰዎች አሉ፡፡”

ሾልኮ የወጣው ሰነድ፣ የዮርዳኖሱ ንጉሥ አብዱላ ፣ዩናይትድ ስቴትስና እንግሊዝ ውስጥ ፣ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት በሚስጥር የናጠጠ ሀብት ያፈሩ መሆኑን ያሳያል፡፡

አብዱላ ግን ሀብታቸው ለመደበቅ መሞከራቸውን አስተባብለዋል፡፡

“ከማንም የምደብቀው ምንም ነገር የለኝም፡፡ ለማንኛውም ግን እኛ ከዚህም በላይ ነን፡፡ ዮርዳኖስ የጥቃት ዒላማ ስትደረግ ይህ የመጀመሪያዋ አይደለም፡፡”

የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ከኻን፣ ካቢኔ ሚኒስትሮችና ቤተሰቦቻቸውም እንዲሁ፣ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ ሀብቶችን ከባህር ማዶ ባሉ ኩባንያዎች ማስቀመጣቸውም ተጋልጧል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ከኻን “ምርመራ ይካሄድበታል” ብለዋል፡፡

የቼክ ጠቅላይ ሚኒስትር አንድሬጅ ባቢስ፣ ማንነቱ ባልታወቀ የባህር ማዶ ኩባንያ ስም፣ በፈረንሳይ 22 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ ንብረት ገዝተዋል፡፡

ባቢስ በዚህ ሳምንት በሚደረገው ጠቅላላ ምርጫ ይወዳደራሉ፡፡

ባላፈው እሁድ በተደረገው የምርጫ ክርክር ድርጊታቸውን እንዲህ በማለት አስተባብለዋል፡፡

“ገንዘቡ የወጣው ከቼክ ባንክ ነው፡፡ ገንዘቡ ቀረጥ ተከፍሎበታል፡፡ የራሴ ገንዘብ ነበር፣ ወደ ቼክ ሪፐብሊክ ይመለሳል፡፡”

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡኹሩ ኬኒያታ እና ስድስት የሚደርሱ ቤተሰቦቻቸው በውጭ በርካታ ድርጅቶች ያላቸው መሆኑም ተመዝግቧል፡፡ ከእነዚህ ሀብቶች ውስጥ አንደኛው ከ30 ሚሊዮን ዶላር በላይ ያወጣል፡፡

ይሁን እንጂ የኬኒያታ ቤተሰቦች የመንግሥትን ሀብት ስለመሰርቃቸው የቀረበ ማስረጃ ግን የለም፡፡ በፓንዶራ ፔፐር ከተመዘገቡ በርካታ ሀብቶቻቸው መካከል ከባህር ማዶ ያሉትን ጨምሮ ብዙዎቹ በህጋዊ መንገድ የተመዘገቡ ናቸው፡፡

ዓለም አቀፉ የግልጽነትና ጸረ ሙስና ዘመቻ የእንግሊዙ ተሟጋች ቡድን ኃላፊ ርቸል ዴቪስ ተካ ፣ በበሰነዱ የተጋለጡ በርካታ ሀብቶችን “የሚያስተሳስራቸው አንድ ክር አለ” ይላሉ፤ እሱም “ለንደን ነው፡፡”

“በእንግሊዝ ዋና ከተማና ከሱም ጋር የተያያዙ እንደ ብሪትሽ ቨርጂን አይላንድ የመሳሰሉት ገንዘቡ የማን እንደሆነ በመደበቅ ህጋዊ ከለላ የሚሰጡ መዋቅሮች አሉ፡፡” የሚሉት ርቸል እንዲህ ብለዋል

“በአሁኑ ወቅት ሚስጥራዊ በሆነና ከባህር ማዶ በተዘመገበ ድርጅት ከተጠቀሙ ማንነትዎን ሳይገልጹ ንብረት መግዛት ይችላሉ፡፡ ለዓለም አቀፉ ልሂቃን የቅንጦት አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትም አሉን፡፡ በጣም በሚያሳዝን መልኩ እነዚህ ሙሰኞችና የወንጀል ተዋናዮች፣ ገንዘቦቻቸውን በህገወጥ መንገድ እንዲያዘዋውሩና የተመዘበረ ሀብቶቻቸውን እንዲያስተዳደሩ በደስታ ለመርዳት፣ ፈቃደኞች የሆኑ የሂሳብ ሰራተኞች ወይም አካውንታት፣ የህግ ባለሙያዎች የሪል ስቴት ኤጀንቶችና የመሳሰሉ በርካታ ባለሙያዎች አሉ፡፡”

ለእንግሊዝ የወግ አጥባቂው ፓርቲ የሚለግሱ ባለሀብቶች ከተጋለጠው ድርጊት ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ ከቀረበ በኋላ ገዥው ፓርቲ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱ ተገልጿል፡፡

ቻንሰርል ሪሽ ሱንካ ትላንት ሰኞ በሰጡት መግለጫ ፣ “ለንደን ከታክስ በመሸሽ የጎደፈው ስም አላት” የሚለው ክስ “አሳፋሪ” ነው ብለዋል፡፡

“መንግሥት ዓለም አቀፍ ሙስናን በመዋጋት ረገድ ያለው ሪከርድ በጣም ጠንካራ ነበር” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG