በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደህንነት ተቋሙ ከኮቪድ-19 እፎይታ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር ተሰርቋል አለ


ፎቶ ፋይል፦ የሥራ ቅጥር አካባቢ ሰዎች ሲዘዋወሩ
ፎቶ ፋይል፦ የሥራ ቅጥር አካባቢ ሰዎች ሲዘዋወሩ

የዩናይትድ ስቴትስ የሚስጥር ደህንነት አገልግሎት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሥራቸውን ላጡ ሰዎችና የንግድ እንቅስቃሴያቸው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ድርጅቶች መረጃ ወይም እንዲውል ከተመደበው የእፎይታ በጀት ፕሮግራም ውስጥ ቢያንስ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር የሚሆን ገንዘብ መሰረቁን አስታወቀ፡፡

ምንም እንኳ ተሰርቋል የተባለው ገንዘብ ለኮቪድ 19 ከዋለው ሶስት ከመቶ ያህሉን ብቻ ቢሆንም ይህም ሆኖ የገንዘቡ መጠን ከፍተኛ መሆን አሳሳቢ መሆኑ ትናንት በወጣው መግለጫ ተገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ ተሰርቋል የተባለው ግምት በሚስጥር ደህንነቱ አካል መረጃዎች ብቻ የተገኘ ሲሆን ከሥራ ሚኒስቴርና ከአነስተኛ የንግድ አገልግሎት ሰጭ ድርጅቶች አስተዳደር የተገኙ መረጃዎችን የማይጨምር መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በደህንነት ተቋሙ በወረርሽኙ ወቅት የተጭበረበሩ ብሄራዊ ሀብቶችን ተከታትሎ የማስመለሱን ፕሮጀክት የሚመሩት ሮይ ዶትሰን በተቋማቸው ምርመራ እየተካሄደባቸው የሚገኙ ከ900 በላይ የወንጀል ድርጊቶች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG