በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓናማው ፕሬዚዳንት የደም በሽታ


ፎቶ ፋይል፦ የፓናማ ፕሬዚዳንት ላውረንቲኖ ኮርቲዞ
ፎቶ ፋይል፦ የፓናማ ፕሬዚዳንት ላውረንቲኖ ኮርቲዞ

የፓናማ ፕሬዚዳንት ላውረንቲኖ ኮርቲዞ ያልተለመደ ዓይነት የደም በሽታ እንዳለባቸው ትናንት ሰኞ አስታወቁ።

የ69 ዓመቱ ኮርቲዞ በሰጡት መግለጫ "የአሳሳቢነት ደረጃው መካከለኛ" የሚባል ማይሎ-ዲስ-ፕላስቲክ ሲንድረም እንዳለባቸው የታወቀው ባለፈው የግንቦት ወር መደበኛ የጤና ምርመራ ባደረጉበት ወቅት የሂሞግሎቢን እና የነጭ የደም ሴል ቆጠራ መቀነስ አሳይቷል።

ማይሎዳይስፕላስቲክ ሲንድረም በአጥንት መቅኒ ውስጥ ደም የሚፈጥሩ ሕዋሳት ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል። የአሜሪካ የካንሰር ማኅበር ማይሎዳይስፕላስቲክ ከካንሰር ህመሞች አንዱ አድርጎ ይወስደዋል።

በዘገባው እንደተጠቆመው ኮርቲዞ እአአ ሃምሌ 1 ለአገራቸው ብሄራዊ ምክር ቤት ዓመታዊ ንግግራቸውን ካሰሙ በኋላ ተጨማሪ የልዩ ባለ ሞያ አስተያየት ለማግኘት ባለሙያተኛ ሁለተኛ አስተያየት ወደ ሂዩስተን፣ ቴክሳስ ያቀናሉ።

XS
SM
MD
LG