በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም መሪዎችን ሃብትና ሙስና የሚያጋልጥ ሰነድ ፓናማ ከሚገኝ ኩባኒያ ሾልኮ ወጣ


ሞሳክ ፎንሴካ ከተባለ የህግ ኩባኒያ
ሞሳክ ፎንሴካ ከተባለ የህግ ኩባኒያ

በሁሉም የዓለም ማዕዘናት ያሉ ከርቴዎችን የገንዘብ ዝውውር የሚያሳየው በሚነካው በዚህ ሰነድ የበርካታ የዓለም መሪዎች ስም ተጠቅሷል።

ፓናማ ከሚገኘው ሞሳክ ፎንሴካ ከተባለ የህግ ኩባኒያ የወጡት አስራ አንድ ሚሊዮን ሰነዶች ናቸው። ሰነዶቹ ባለ ብዙ ገንዘብ፣ እና ባለ ብዙ ጉልበትና ስልጣን ግለሰቦች ግብር እንዳይከፍሉ፣ ሙስናቸው እንዳይደረስበት ደግሞ ከተጣሉባቸው ማእቀቦች ለማምለጥ ሃብታቸውን እንዴት አድርገው ፓናማን በመሳሰሉ መሸሸጊያዎች እንደሚደብቁ የሚያጋልጡ መሆናቸውን ጸረ ሙስና ተሟጋቾች ይናገራሉ።

የዓለም መሪዎችን ሃብትና ሙስና የሚያጋልጥ ሰነድ ፓናማ ከሚገኝ ኩባኒያ ሾልኮ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:41 0:00

የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል ባልደረባ ማጊ መርፊ "ሰነዶቹ የሚያሳዩን ማንነታቸው እንዳይታወቅ የሚፈልጉ ሰዎች በተለያዩ ሀገሮች በጣም በቀላሉ በሚስጥር ኩባኒያ ማቋቋም እንደሚችሉ ነው። ያን የሚያደርጉት ከገንዘቡ ጋር ስማቸው እንዳይነካካ ለመደበቅ ነው።" ብለዋል

ከፓናማው ፎሳክ ፎንሴካ ኩባኒያ በድብቅ በወጡት ሰነዶች ውስጥ ከሃምሳ የዓለም ሃገሮች የሆኑ ኣንድ መቶ ኣርባ ሶስት ፖሌቲከኞች ስም የተገኘ ሲሆን ከመካከላቸው ኣስራ ሁለቱ ሮሳነ ብሔራት ናቸው።

የአይስላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሲግመንደር ገንላግሰን በውጭ ሃገር በተቋኣቋመ ኩባኒያ አማካይነት በሀገራቸው ባንኮች ውስጥ ብዙ ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ነዋይ እንደሚያንቀሳቅሱ የሚያሳይ ሰነድ ብቅ ያለ ሲሆን ከስልጣን እንዲወርዱ ጥያቄ መጥቶባቸዋል።

የፓናማው ሰነድ የቻይና የፕሬዚደንት ሺ ፒንግ ቤተሰብ እና ከፍተኛ የኮሙኒስት ፓርቲው ሹማምንት ስምም አጋልጡዋል። የአርጀንቲና ፕሬዚደንት ሞሪሲዮ ማክሪ ገንዘባቸው ባሃማስ ውስጥ ተደብቁዋል ተብለዋል። የዩክሬይኑ ፕሬዚደንት ፔትሮ ፖሮሼንኮም እ.አ.አ. በ2014 ዓ.ም. በሩስያ ከሚደገፉት ተገንጣይ ሓይሎች ጋር ወታድሮቻቸው ከባድ ፍልሚያ ላይ በነበሩበት ሰዓት ብሪቲሽ ቨርጂን አይላንድስ በምትባለው ደሴት ገንዘብ የሚደብቁበት ኩባኒያ ማቋቋማቸውን ሰነድቹ አጋልጠዋል።

የሩስያ ፕሬዚደንት ቪላዲሚር ፑቲን የቀርብ ረዳቶች በሚመሩት እና በአሁኑ ጊዜ በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ ህብረት ማዕቀብ ስር ባለው ባንክ ሩሲያ አማካኝነት በህጋዊ አካል ሽፋን የብዙ ቢሊዮን ዶላር ህገ ወጥ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ አካል መኖሩን ሰነዱ ጠቁሙዋል።

የፓናማው የህግ ኩባኒያ ሞሳክ ፎንሴካ የጣስኩት ህግ የለም በማለት አጥብቆ አስተባብሏል። ጸረ ሙስና ተሟጋቾች ግን ምርመራ እንዲቀጥል ጠይቀዋል ። የግሎባል ዊትነሱ ሮበርት ፓልመር "ህገ ወጥ ገንዘብ ህጋዊ ስም አልብሶ ማንቀሳቀስ፣ ከማዕቀብ ለመደበቅ ወይም ከግብር ክፍያ ለማምለጥ የተፈጸመ ተግባር ከሆነ ህገ ወጥ ድርጊት ለመሆኑ አንድና ሁለት የለውም። ይህ ኩባኒያ ዓለም አቀፍ ማዕቀብ የተደነገገባቸው ከሃያ ሶስት የሚበልጡ ደምበኞች እንዳሉት ተመልክተናል።" ብለዋል።

ከፓናማው ኩባኒያ ከወጡት ብዛት ያላቸው ሰነዶች ኣብዛኞቹ በዓለም ዙሪያ ያሉ ግለሰብ ቱጃሮች የክብረታቸው ልክ እንዳይታወቅ ለመደበቅ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያሳዩ ናቸው። አሁንም የትራንስፓሬንሲ ኢንተርናሺናልዋ ማጊ መርፊ "ገንዘቡን በዓለም የገንዘብ ተቋማት መረብ ውስጥ እንዲዘዋወር የባንክ ባለሙያዎች፣ ጠበቆች፣ እና የሂሳብ ባለሙያዎችን ተሳትፎ ይጠይቃል። እንግዲህ፣ እዚህ ለንደን ከተማ ውስጥ ያለን ሰዎች የሙስና ገንዘብ ሲንቀሳቀስ ሚና በመጫወት ደስተኞች ነን ወይ? ያ የብሪታንያ መንግስትም ሆነ ሌሎች መልስ ሊሰጡበት የሚገባ ከባድ ጥያቄ ነው።" ብለዋል።

ለዚህ ጥያቄ በመጪው ግንቦት ወር የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምረን በሚያስተናግዱት የጸረ ሙስና ጉባዔ ላይ የሚካፈሉት የዓለም መሪዎች መልሱን ይፈልጉለታል ።

በፓናማው ሰነድ የዴቪድ ካምረን ወግ አጥባቂ ፓርቲ በርካታ አባላትም ስም ተጠቅሷል። ሟቹ አባታቸውም አልቀሩ፣ የቤተሰባቸውን ሃብት በባሃማስ ኩባኒያ ስም ሸሽገዋል ይላል።

ሄንሪ ሪጅዌል ከለንደን ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል። ቆንጂት ታዬ አቅርባዋለች ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የዓለም መሪዎችን ሃብትና ሙስና የሚያጋልጥ ሰነድ ፓናማ ከሚገኝ ኩባኒያ ሾልኮ ወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG