በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከኢትዮጵያ የተወሰደ ቡና ፓናማ ውስጥ በኩባያ ከ100 ዶላር በላይ በመሸጥ ላይ ነው


ፎቶ ፋይል፦ ፓናማ፤ ታህሣስ እአአ 28/2017 , Dec. 28, 2017.
ፎቶ ፋይል፦ ፓናማ፤ ታህሣስ እአአ 28/2017 , Dec. 28, 2017.

በ1960ዎቹ ከኢትዮጵያ ተወስዶ ፓናማ ውስጥ መብቀል የጀመረው የቡና ዓይነት፣ በዋና ከተማዋ አንድ ኩባያ ከመቶ ዶላር በላይ በመሸጥ ላይ ነው ተብሏል፡፡

በአገሪቱ የቡና ተክል ላይ ችግር የፈጠረውን ፈንገስ ወይም ሸጋታ መቋቋም የሚችለው ጌይሻ የተሰኘው ከኢትዮጵያ የሄደው የቡና ዓይነት ተፈላጊና ውድ ሆኗል፡፡

ፓናማ እንደ ብራዚልና ኮሎምቢያ በዓለም ቀዳሚ የቡና አምራች ባትሆንም፣ ከኢትዮጵያ በመጣው ጌይሻ ቡና ምክንያት ግን በዓለም ጥራት ያለው ቡና የምታዘጋጅ አገር አድርጓታል፡፡

በፓናማ ከ70 በላይ የጌይሻ ቡና አምራቾች ሲኖሩ፣ ቁጥራቸው እያደገ ሲመጣ ዋጋው እየጨመረ የመምጣት ዕድል ይኖረዋል ተብሏል፡፡

“ጌይሻ ቡና ለየት ያለ ግሩም ጣዕም ያለውና፣ በኩባያ ከመቶ ዶላር በላይ ማውጣቱ ይገባዋል” ሲሉ ቡና ወዳጆች መናገራቸውን የቪኦኤው ኦስካር ሱልባራን ከፓናማ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG