በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፓናማ አውቶብስ ተገልብጦ 39 ፍልሰተኞች ሞቱ


በፓናማ 60 ፍልሰተኞችን የያዘ አውቶብስ ወደ ገደል ተገልብጦ 39ኙ ሲሞቱ 20 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ የአገሪቱ የፍልሰተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል
በፓናማ 60 ፍልሰተኞችን የያዘ አውቶብስ ወደ ገደል ተገልብጦ 39ኙ ሲሞቱ 20 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ የአገሪቱ የፍልሰተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል

በፓናማ 60 ፍልሰተኞችን የያዘ አውቶብስ ወደ ገደል ተገልብጦ 39ኙ ሲሞቱ 20 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል ሲሉ የአገሪቱ የፍልሰተኞች ጉዳይ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

በአገሪቱ በፍልሰተኞች ላይ የደረሰ አሰቃቂ አደጋ እንደሆነ ሲገለጽ፣ ባለሥልጣናቱ ስለ ተጎጂዎቹና ሟቾቹ ዜግነት ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው 20 ፍልሰተኞች ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል፡፡

አውቶብሱ ኮሎምቢያን ከማዕከላዊ አሜሪካ ጋር በሚያገናኘው አደገኛና ገደል መንገድ ላይ ሲጓዝ እንደነበርና ወደ ስደተኞች መጠለያ እያመራ እንደነበር ታውቋል፡፡

ባለፈው ዓመት 248 ሺህ የሚሆኑ ፍልሰተኞች በአደገኛው መንገድ ላይ መጓዛቸውና አብዛኞቹ ቬንዝዌላውያን እንደነበሩ ተገልጿል።

የአሜሪካ አዲሱ የፍልሰተኞች ህግ ጠበቅ በማለቱ፣ አብዛኞቹ ወደ ፓናማ ለመመለስ ተገደዋል፡፡ ወደ ቬንዝዌላ ለመመለስ መጓጓዣው ውድ ይሆንባቸዋል ተብሏል፡፡

በያዝነው የፈረንጆች ዓመት ብቻ 32 ሺህ 800 ፍልሰተኞች በገደላማው መንገድ ማለፋቸውን የፓናማ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG