በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዛ ግጭትና ውጥረት እንደቀጠለ ነው

የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሣሌም ይዛወር በነበረ ጊዜ ከእሥራኤል የፀጥታ ኃይሎች ጋር ከትናንት በስተያ በተካሄዱ የድንበር ላይ ግጭቶች ከተገደሉ ፍልስጥዔማዊያን መካከል የተወሰኑትን አስከሬኖች ለመቅበር አደባባይ የወጡ በሺሆች የሚቆጠሩ ፍልስጥዔማዊያን እንደሚበቀሉ ዝተዋል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ወደ ኢየሩሣሌም ይዛወር በነበረ ጊዜ ከእሥራኤል የፀጥታ ኃይሎች ጋር ከትናንት በስተያ በተካሄዱ የድንበር ላይ ግጭቶች ከተገደሉ ፍልስጥዔማዊያን መካከል የተወሰኑትን አስከሬኖች ለመቅበር አደባባይ የወጡ በሺሆች የሚቆጠሩ ፍልስጥዔማዊያን እንደሚበቀሉ ዝተዋል።

ስድሣ ፍልስጥዔማዊያን የተገደሉበትንና 2 ሺህ 7 መቶ የቆሰሉበትን ይህንን ጥቃት የተባበሩት መንግሥታት ባለሥልጣናት “የጭካኔ አድራጎት” ሲሉ አውግዘውታል።

ትናንት ለቀብር የወጡት ፍልስጥዔማዊያን ኀዘንተኞች “በመንፈስና በደም ሰማዕትነታችሁን እንጠብቀለን” እያሉ ዘምረዋል።

በጋዛና በእሥራኤል አዋሣኝ አካባቢዎችና በዌስት ባንክ ትናንትም ፍልስጥዔማዊያኑ በወታደሮቹ ላይ ድንጋይ ሲወረውሩና እሣት ሲያቀጣጥሉ ወታደሮቹ አስለቃሽ ጋዝ ሲተኩሱባቸው እንደነበረ ተገልጿል።

በትናንት ግጭቶች ቢያንስ ሁለት ፍልስጥዔማዊያን መገደላቸው ተዘግቧል።

የእሥራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ሃገራቸው ድንበሮቿን የማስከበር መብት እንዳላት በመግለፅ እርምጃውን የተከላከሉ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ደግሞ ቀደም ሲል በሽብር ድርጅትነት የፈረጀችው ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስ ተቃውሞዎቹን መሆኑን በመግለፅ በፍልስጥዔማዊያኑ ላይ የተፈጠረው ግድያ እንዲጣራ ለፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤቱ የቀረበን የውሣኔ ሃሣብ ረቂቅ አግዳለች።

የፍልስጥዔሙ ፕሬዚዳንት ማኅሙድ አባስ የእሥራኤልን እርምጃ “ጭፍጨፋ” ሲሉ ጠርተውታል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG