በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የእስራኤል ወታደሮች በዌስት ባንክ ባካሄዱት ወረራ 7 ሰዎች ገደሉ - የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት


የእስራኤል የጦር መኪኖች በዌስት ባንክ የጄኒን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ወረራ የፈፀመ ሲሆን በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ታጥቂዎች ጋር ውጊያ አካሂዷል፤ እአአ ግ ንቦት 21/2024
የእስራኤል የጦር መኪኖች በዌስት ባንክ የጄኒን የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ወረራ የፈፀመ ሲሆን በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ታጥቂዎች ጋር ውጊያ አካሂዷል፤ እአአ ግ ንቦት 21/2024

የእስራኤል ጦር በቁጥጥሩ ስር በሚገኘው ዌስት ባንክ ማክሰኞ እለት ወረራ የፈፀመ ሲሆን፣ በደቡባዊ ጋዛ ሰርጥ ከሐማስ ታጥቂዎች ጋር ውጊያ አካሂዷል።

የፍልስጤም የጤና ባለስልጣናት የእስራኤል ወታደሮች ዌስት ባንክ በሚገኘው ጄኒን ከተማ ባካሄዱት ወረራ ሰባት ሰዎች መግደላቸውን ያስታወቀ ሲሆን፣ የጄኒን መንግስት ሆስፒታል ከተገደሉት ሰዎች መካከል አንዱ የቀዶ ጥገና ሐኪም መሆኑን አመልክቷል።

የእስራኤል ጦር በበኩሉ በታጣቂዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መፈፀሙን እና ወታደሮቹ በርካታ ተዋጊዎችን ተኩሰው መግደላቸውን ገልጿል።

በሌላ በኩል የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ከፍተኛ አቃቤ ህግ በጋላንት እና በጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለመጠየቅ የወሰደውን እርምጃ ውድቅ አድርጓል።

ጋላንት ማክሰኞ እለት ባወጡት መግለጫ በእሳቸው እና በኔታንያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ለማውጣት የቀረበውን ማመልከቻ "አሳፋሪ" ሲሉ ጠርተውታል።

"አቃቤ ህግ ካሪም ካን፣ የእስራኤልን መንግስት እራስን የመከላከል እና ታጋቾችን የማስለቀቅ መብት ለመከልከል ያደረጉት ሙከራ ውድቅ መደረግ አለበት" ሲሉ ጋላንት በኤክስ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ አመልክተዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG