በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ የፓኪስታን ጠ/ር የሰባት ዓመት እሥራት ተፈረደባቸው


ፎቶ ፋይል:-የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ
ፎቶ ፋይል:-የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ

የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ በይፋ ከሚታወቅ የገቢ ምንጭ ውጭ ንብረት ይዘዋል ያለ አንድ የሃገሪቱ ፀረ-ሙስና ችሎት ዛሬ የሰባት ዓመት እሥራት ፈርዶባቸዋል።

የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ በይፋ ከሚታወቅ የገቢ ምንጭ ውጭ ንብረት ይዘዋል ያለ አንድ የሃገሪቱ ፀረ-ሙስና ችሎት ዛሬ የሰባት ዓመት እሥራት ፈርዶባቸዋል።

እዚያው ኢስላማባድ በተሰየመው ችሎት ላይ የነበሩት የስድሣ ስምንት ዓመቱ ሸሪፍ በተመሠረቱባቸው ሁለት ክሦች ላይ ዳኞች ውሣኔ እንዳሰሙ እጃቸው ተይዞ ታስረዋል።

ለሦስት የሥልጣን ዘመናት የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት ናዋዝ ሸሪፍ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ የከፈቱን የብረታ ብረት ፋብሪካ ገንዘብ ከየት እንዳመጡት ማሳወቅ ባለመቻላቸው ጥፋተኛነት የተበየነባቸው ሲሆን በሁለተኛው ዶሴ ግን የቀረበባቸው ማስረጃ በቂ አይደለም በሚል ክሡን ዳኞቹ ዘግተውታል።

ናዋዝ ሸሪፍ በተጨማሪም የሃያ አምስት ሚሊየን ዶላር ቅጣት የተጣለባቸው ሲሆን ለአሥር ዓመታት ከፖለቲካ ውጭ ሆነው እንዲቆዩም ተፈርዶባቸዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG