በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ አፍጋኒስታን ድንበር ላይ የወሰደችው ሰው አልባ የአየር ጥቃት

ዩናይትድ ስቴትስ፣ አፍጋኒስታን ድንበር ላይ በቅርቡ በወሰደችው ሰው አልባ የአየር ጥቃት ከተገደሉት ነውጠኞች አንደኛው የታሊባን ምክትል ኃላፊ መሆኑን እራሱ ህገ ወጡ ቡድን ታሊባን ዛሬ ሰኞ በሰጠው ማረጋገጫ አስታወቀ።

ዩናይትድ ስቴትስ፣ አፍጋኒስታን ድንበር ላይ በቅርቡ በወሰደችው ሰው አልባ የአየር ጥቃት ከተገደሉት ነውጠኞች አንደኛው የታሊባን ምክትል ኃላፊ መሆኑን እራሱ ህገ ወጡ ቡድን ታሊባን ዛሬ ሰኞ በሰጠው ማረጋገጫ አስታወቀ።

የምክትል ኃላፊውን ካሃን ሰኢድ ሳጀና መሞት ይፋ ያደረገው የቡድኑ አፈቀላጤ፣ ሰውአልባው ጥቃት የተካሄደው ባለፈው ሐሙስ በሰሜን ዋዚሪስታኗ አካባቢ ጎረዊክ ውስጥ ነው ብሏል።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ብዙውን ጊዜ፣ ፓኪስታን ውስጥ ስለሚካሄደው ፀረ ሽብርተኛነት ሰው አልባ የአየር ጥቃት አስተያየት ከመስጠት የተቆጠቡ በመሆናቸው፣ የአካባቢው የደኅንነት ባለሥልጣናት እንዳረጋገጡት፣ ሟቹ ሳጀና እና ተዋጊዎቹ፣ በመጠለያነት ከቆዩባት ከኮሆስት ክፍለሀገር ወደ መኖሪያችው እየተመለሱ ነበር።

ሳጀና በዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች ላይ ባካሄደው የሽብርተኛነት ጥቃት በዋሺንግተን እየተፈለገ እንደነበርም ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG