በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዚደንት ትረምፕ ፓኪስታን ለአሸባሪዎች ከለላ እየሰጠች ነው አሉ


ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ፓኪስታን ለሽብርተኛች ከለላ ትሰጣለች ሲሉ በትዊተር ያስተለፉትን መልዕክት በተመለከተ፣ ኢስላማባድ አገሯ ላይ ለሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ተቃውሞዋን አሰማች።

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ፣ ፓኪስታን ለሽብርተኛች ከለላ ትሰጣለች ሲሉ በትዊተር ያስተለፉትን መልዕክት በተመለከተ፣ ኢስላማባድ አገሯ ላይ ለሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሰደር ተቃውሞዋን አሰማች።

የአሜሪካ ኃይሎች አፍጋኒስታን ውስጥ እየተዋጓቸው ያሉትን አሸባሪዎች ፓኪስታን ከለላ እየሰጠች መሆኗን በመጥቀስ ነበር፣ የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ ፓኪስታንን የወነጀሉት።

ኢስላማባድ ውስጥ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምበሲ ቃል አቀባይ እንደገለጸው፤ አምባሳደር ዴቪድ ሃሊ፣ ወደ ፓኪስታን ውጪ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በመሄድ፣ ትራምፕ ትናንት ሰኞ ስላስተላለፉት የአዲስ ዓመት የመግቢያ ንግግርቸው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፕሬዚደንት ትረምፕ፣ ትናንት ለገባው አዲስ ዓመት፣ የመጀመሪያቸው በሆነው የትዊተር መልዕክታቸው፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሞኝነት ባለፉት 15 ዓመታት ለፓኪስታን ከ$33 ቢልዬን በላይ መስጠቷን አስታወሰው፣ በምትኩ ለእኛ ግን ከውሸትና ከማታለል ሌላ የሰጡን ነገር የለም ነበር ያሉት።

"አፍጋኒስታን ውስጥ ለምናድናቸው ሽብርተኞች አስተማማኝ የሆነ መሸሸጊያ መስጠን ተያይዘውታል አሁን ግን ያ ያከትማል" ብለዋል ፕሬዚደንት ዶናልድ ትረምፕ

ትረምፕ በዚያ አነጋገራቸው፣ ለኢራን የሚሰጠውን የገንዘብ እርዳታ ለማቋረጥ ማቀዳቸው ይሁን ግልፅ አይደለም።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG