በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፓኪስታን በእስር ላይ ያለውን የህንድ ተዋጊ ጄት አብራሪ ልትፈታ ነው


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

ፓኪስታን፣ ተማርኮ በእስር ላይ ያለውን የህንድ ተዋጊ ጄት አብራሪ ልትፈታ መሆኗን አስታወቀች።

ፓኪስታን ቀደም ሲል በሰጠችው መግለጫ፣ ሁለት የህንድ አየር ኃይል ተዋጊ ጄቶች “ድንበሬን ጥሰው ገብተዋል” በማለት ጥቃት ማድረሷን አመልክታለች።

በዚሁ ጥቃት ነው፣ ፓይለቱ ያበረው የነበረው አውሮፕላን በፓኪስታን ይዞታ ሥር ባለው ካሽሚር ተመትቶ ሲከሰከስ አብራሪው የተማረከው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኢመራን ከሃን ዛሬ ሐሙስ ለምክር ቤታቸው ባሰሙት ቃል፣ ከህንድ ጋር ላለው ሰላም ምሳሌ ይሆን ዘንድ፣ ፓይለቱን ነገ ዐርብ ወደ ህንድ እንደሚልኩ አስታውቀዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG