በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞው የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር አስር ዓመት እስር ተፈደባቸው


ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን
ፎቶ ፋይል፦ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካን

የፓኪስታን ልዩ ፍርድ ቤት፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኢምራን ካን፣ 'ሥልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር የተያያዘ ብሔራዊ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አዝረክርከዋል' በሚል ለተከሰሱበት ወንጀል፣ ዛሬ ማክሰኞ በ10 ዓመት እስራት እንዲቀጡ ፈርዷል።

ካን በበኩላቸው፣ አገራቸው “ከዩናይትድ ስቴትስ ተጽዕኖ የፀዳ የውጭ ፖሊሲ” እንዲኖራት በመገፋፋታቸው እና በፓኪስታን ጦር ሠራዊት እገዛ መንግሥታቸውን ለመጣል ዋሽንግተን የተጫወተችውን ሚና በሚያሳይ ዲፕሎማሲያዊ መረጃ፣ መወንጀላቸውን ጠቅሰው ሞግተዋል። ይሁን እንጂ ዋሽንግተን እና የፓኪስታን ጦር ሠራዊት የካን’ን ክስ አስተባብለዋል።

በካን አስተዳደር ወቅት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው የነበሩት ሻህ መህሙድ ኩሬሺ’ም ከሚስጥራዊ መረጃ ብክነት ጋር ተያይዞ በተመሰረተ ክስ በተመሳሳይ የ10 ዓመት የእስር ቅጣት ተፈርዶባቸዋል።

እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በሚያዝያ 2022 ዓ.ም በተቃዋሚዎች ጥምረት ከሥልጣን የተወገዱት የ71 ዓመቱ የቀድሞ የፓኪስታን ጠቅላይ ሚንስትር ‘ምስጢራዊ መረጃ አባክነዋል’ የሚለውን ክስ ‘ለፖለቲካዊ ዓላማ ሲባል ከፍተኛ ተሰሚነት ባለው በሃገሪቱ ወታደራዊ ኃይል የተቀነባበረ ነው’ ሲሉ ውድቅ አድርገውታል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG