በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓኪስታን ጎርፍ ከባድ ቀውስ ፈጥሯል


ከባድ ዝናብን ተከትሎ በጎርፍ የተጥለቀለቀ ገበያ ባጃራ መንደር፣ በማንቻር ሀይቅ ዳርቻ፣ በሴህዋን፣ ፓኪስታን፣ 9/6/2022
ከባድ ዝናብን ተከትሎ በጎርፍ የተጥለቀለቀ ገበያ ባጃራ መንደር፣ በማንቻር ሀይቅ ዳርቻ፣ በሴህዋን፣ ፓኪስታን፣ 9/6/2022

በቅርቡ በፓኪስታን የደርሰውን ከባድ ጎርፍ ተከትሎ የአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በከፍተኛ ውሃ በመጥለቅለቁ የእርዳታ ሰራተኞች በሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቃዮችን የሚያሰፍሩበት ደረቅ መሬት ማግኝት መቸገራቸውን የአገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ፡፡

የዝናቡ ወቅት ከጀመረበት ካለፈው ሰኔ አጋማሽ ጀምሮ ሳያቋርጥ የጣለው ዶፍ ዝናብ በፓኪስታን የቅርብ ጊዜ ታሪክ ከፍተኛው ነው ተብሏል፡፡

200 ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ካላት የደቡብ እስያዪቱ አገር አንድ ሦስተኛው ህዝብ በጎርፉ አደጋው ተመቷል፡፡

የአየር ንብረት ለውጥ ሚኒስትር ሸሪ ሬህማን ለሪፖርተሮች በሰጡት መግለጫ በፓኪስታን በስተደቡብ የምትገኘው ሲንዲ ግዛት መዲና ከሆነቸው ካራቺ ወጣ ብለው ባሉ አካባቢዎች በሙሉ፣ የጎርፉ ውሃ አሁንም እንደተኛ ነው፡፡

ከፓኪስታን 160 አውራጃዎች 81 በሚሆኑት ውስጥ በጎርፍ ለተጠቃው 33 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኳይ የጤና እርዳታ ማቅረብ በአገሪቱ ያለው አጣዳፊ ተግባር ነው ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ ከፓኪስታን ህዝብ ጎን መቆማቸውን ለማሳየት በዚህ ሳምንት ፓኪስታን ይገባሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG