በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሕንድ ሩሲያ ሠራሽ የአየር መከላከያ ሥርዓት መግዛቷ እንዳሳሰባት ፓኪስታን አስታወቀች

ሕንድ ሩሲያ ሠራሽ የአየር መከላከያ ሥርዓት መግዛቷ እንዳሳሰባት ፓኪስታን አስታወቀች። ሕንድ ከሩሲያ ላይ ኤስ - 400 ትረምፍ መከላከያዎችን በመያዟ ምክንያት ስላደረባት ሥጋት ኢስላማባድም ተመጣጣኝ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

ሕንድ ሩሲያ ሠራሽ የአየር መከላከያ ሥርዓት መግዛቷ እንዳሳሰባት ፓኪስታን አስታወቀች። ሕንድ ከሩሲያ ላይ ኤስ - 400 ትረምፍ መከላከያዎችን በመያዟ ምክንያት ስላደረባት ሥጋት ኢስላማባድም ተመጣጣኝ እርምጃ እንደምትወስድ ዝታለች።

ሩስያና ሕንድ በቅርቡ የተፈራረሙት የ5 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር የተምዘግዛጊ ሚሣይል መከላከያ ሥርዓት እጅግ የረቀቀ እንደሆነ ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ሕንድ የአየር ክልሏን ከቻይናና ከፓኪስታን ጥቃት ለመከላከል ስትል እየገዛች ያለችው የከፍተኛ ሥፍራዎች መሣሪያ እንደሆነ ኒው ዴልሂ አስታውቃለች።

አድራጎቱ ደቡብ እሥያን ወደ አዲስ የጦር መሣሪያ እሽቅድምድም ሊወስድ የሚችልና አካባቢውን ወዳለመረጋጋት የሚወስድ ነው ሲል የፓኪስታን መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል። ሩሲያ ሠራሽ የሆነው የመከላከያ ሥርዓት ከማንኛውም የአየር ጥቃት መጠበቅና ከሰላሣ ኪሎ ሜትር ከፍታ እስከ 4መቶ ኪሜ ሊወነጨፉ የሚችሉ ሚሣይሎችን ማቆም የሚችል የተራቀቀ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ታውቋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG