በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቻይና በአፍጋኒስታን ፖለቲካ


የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ማኅሙድ ቁሬሺ
የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ማኅሙድ ቁሬሺ

ዩናይትድ ስቴትስ አፍጋኒስታን ውስጥ ያዘመተችውን ጦሯን እንደምትቀንስ እያሳወቀች ባለችበት ወቅት ፓኪስታን "ጠንካራ ወዳጇ ነች" ከምትባለው ቻይና ጋር በተለዋዋጩ የአፍጋኒስታን ፖለቲካ ላይ አዳዲስ ንግግሮችን መጀመሯ ተገለፀ።

ዩናይትድ ስቴትስ አፍጋኒስታን ውስጥ ያዘመተችውን ጦሯን እንደምትቀንስ እያሳወቀች ባለችበት ወቅት ፓኪስታን “ጠንካራ ወዳጇ ነች” ከምትባለው ቻይና ጋር በተለዋዋጩ የአፍጋኒስታን ፖለቲካ ላይ አዳዲስ ንግግሮችን መጀመሯ ተገለፀ።

የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሻህ ማኅሙድ ቁሬሺ ዛሬ ወደ ቤጂንግ ሄደው ከቻይና አቻቸው ዋንግ ዪ ጋር ባደረጉት የሙሉ ቀን ውይይት ሁለቱም ወገኖች በአፍጋን-መርና በአፍጋን ባለቤትነት የሰላም ሂደት እንደሚያምኑ ማሳወቃቸውን የኢስላማባድ ባለሥልጣናት አመልክተዋል።

ፓኪስታን ባለፈው ሣምንት የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስና በታሊባን መካከል የተካሄደ ባለሥልጣናቱ “ፍሬያማ” ያሉትን ውይይት ማመቻቸቷ ተዘግቧል።

ከቻይና አቻቸው ጋር ከተገናኙ በኋላ የፓኪስታኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሃገራቸው መንግሥታዊ ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ አፍጋኒስታን ውስጥ ባሉ አዳዲስ ሁኔታዎችና በአቡዳቢው ውይይት ላይ መነጋገራቸውን አመልክተዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG